ላለፈው አንድ ዓመት በአዳማ ከተማ ቆይታ የነበረው አጥቂ ወደ ቻምፒዮኖቹ ለማምራት ተቃርቧል።

በሀድያ ሆሳዕና ሁለት ዓመታት እንዲሁም በወልዋሎ አንድ የውድድር ዓመት ካሳለፈ በኋላ ዳግም ወደ ቀድሞ ክለቡ አዳማ ከተማ ተመልሶ ላለፈው አንድ ዓመት በክለቡ ቆይታ የነበረው የፊት መስመር ተጫዋቹ ዳዋ ሆቴሳ በዉሉ አንድ ቀሪ ዓመት እየቀረው በስምምነት ተለያይቶ ወደ ሲዳማ ቡና ለማምራት እጅግ ተቃርቧል።
እግር ኳስን በክለብ ደረጃ በናሽናል ሲሚንቶ ከጀመረ በኋላ በቅዱስ ጊዮርጊስ ከዛ ቀጥሎም በሦስት አጋጣሚዎች አዳማ ከተማ፣ ሀድያ ሆሳዕና እና ወልዋሎ እንዲሁም በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በተለያዩ የዕድሜ እርከኖች ማገልገል የቻለው ተጫዋቹ በዛሬው ዕለት ዝውውሩን ያገባድዳል ተብሎ ይጠበቃል።

