በጉጉት የሚጠበቀው ጨዋታ በምን የቴሌቪዥን አማራጭ በቀጥታ ይተላለፋል?

በጉጉት የሚጠበቀው ጨዋታ በምን የቴሌቪዥን አማራጭ በቀጥታ ይተላለፋል?

ነገ 10 ሰዓት የሚደረገው የኢትዮጵያ እና ሞዛምቢክ ብሔራዊ ቡድኖች ጨዋታ በቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭት ሽፋን ያገኛል።

በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የምድብ 4ኛ ጨዋታዎች መደረግ የጀመሩ ሲሆን ሀገራችን ኢትዮጵያም በምድብ 10 ተደልድላ ወደ አህጉራዊ ውድድሮች ለመመለስ ያላትን ተስፋ ለማለምለም ነገ ከሞዛምቢክ አቻዋ ጋር ጨዋታዋን ታደርጋለች።

10 ሰዓት የሚደረገውን ይህንን ተጠባቂ ጨዋታም ኤ ዋን ሚዲያ (A One Media) ከካፍ ባገኘው መብት ደረጃውን የጠበቀ ቀረፃ የሚያደርግ ሲሆን እስካሁኗ ሰዓት ድረስ ይህንን ጨዋታ ከካፍ ምስሉን ተቀብለው ለማስተላለፍ ሦስት የቴሌቪዥን ተቋማት መብቱን እንደወሰዱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ሱፐር ስፖርት እና ቢን ስፖርት በአፍሪካ ባላቸው የየራሳቸው የስርጭት ቀጠና ጨዋታውን የሚያስተላልፉ ሲሆን የሀገራችን ተቋም የሆነው ሀገሬ ቴሌቪዥንም ለተመልካቾቹ ጨዋታውን ተደራሽ ለማድረግ መብቱን እንዳገኘ አውቀናል።