በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ወሳኝ የሆነው የነገው የኢትዮጵያ እና ሞዛምቢክ ጨዋታ በምዕራብ አፍሪካዊ አልቢትሮች ይመራል።

በ2027 በምስራቅ አፍሪካ በሚደረገው የአፍሪካ ዋንጫ ለመሳተፍ የምድብ የማጣሪያ ጨዋታዎች እየተደረጉ ይገኛሉ። ሀገራችን ኢትዮጵያም በምድብ 10 ከሴኔጋል፣ ሞዛምቢክ እና ሲዳን ጋር ተደልድላ በምድቡ አንድ ድል አሳክታ ቀጣይ ጨዋታዎቿን እየተጠባበቀች ትገኛለች። ከቀሪ ሦስት ጨዋታዎች ወሳኙ የነገው የሞዛምቢክ ጨዋታም 10 ሰዓት ላይ በባህር ዳር ስታዲየም የሚደረግ ይሆናል። ይህንን ጨዋታም የምዕራብ አፍሪካዊቷ ሀገር ጋምቢያ አልቢትሮች እንደሚመሩት ታውቋል።
በዚህም በመሐል ዳኝነት ላሚን ኤን ጃምሜህ ከረዳቶቹ ናፋሊ ጃርጁ እና ኤሳሃ ሶዌ እንዲሁም ከአራተኛ ዳኛው አብደላህ ኤል ጃሜህ ጋር ወሳኙን ጨዋታ እንደሚመሩት ካፍ አስታውቋል።

