ሲዳማ ቡናዎች ምክትል አሰልጣኝ ቀጥረዋል

ሲዳማ ቡናዎች ምክትል አሰልጣኝ ቀጥረዋል

አሰልጣኝ ያሬድ ገመቹ  አብሯቸው የሚሠራ ረዳት አሰልጣኝ መሾማቸው ታውቋል።

ባሳለፍነው ዓመት የሊጉን ዋንጫ ያነሱት ሲዳማ ቡናዎች በሀገር ውስጥ እና በአፍሪካ መድረክ ለሚያደርጉት ተሳትፎ ጠንካራ ዝውውሮችን በመፈፀም በአፍሪካ ቻምፒዮንስ ሊግ የመጀመርያውን ዙር ማለፋቸው ይታወቃል። የአሰልጣኞች አባላት ቁጥርን ከፍ በማድረግ ራሳቸውን ለማጠናከር በማሰብ አሁን ደግሞ ዳዊት ሀብታሙን የአሰልጣኝ ያሬድ ገመቹ ሌላኛው ረዳት አሰልጣኝ አድርገው መሾማቸው ታውቋል።

በከፍተኛ ሊግ በገጣፎ ለገዳዲ፣ በሀምበርቾ ዱራሜ፣ በጅማ አባ ጅፋር በዋና አሰልጣኝነት የሠራው እንዲሁም በሊጉ በወላይታ ድቻ ፣ በወልቂጤ ከተማ እና ባሳለፍነው ዓመት ደግሞ በአዳማ ከተማ በረዳት አሰልጣኝነት የሠራው ባለ ብዙ ልምዱ ዳዊት ሀብታሙ አሁን የአሰልጣኝ ያሬድ ገመቹ ምክትል በመሆን መሾሙን አውቀናል።