የሀዲያ ሆሳዕና የተጫዋቾች ተገቢነት ጥያቄ ውድቅ ተደርጓል

የሀዲያ ሆሳዕና የተጫዋቾች ተገቢነት ጥያቄ ውድቅ ተደርጓል

በተመስገን ብርሃኑ እና በፀጋአብ ግዛው ጉዳይ ፌዴሬሽኑ ውሳኔ አሳልፏል።

ሶከር ኢትዮጵያ ከዚህ ቀደም ባቀረበችው ዘገባ ፀጋአብ ግዛው እና ተመስገን ብርሃኑ ወደ ቅዱስ ጊዮርጊስ ያደረጉትን ዝውውር አስመልክቶ ሀዲያ ሆሳዕና በክለቡ ስራ አስኪያጅ አቶ አባተ ተስፋዬ በኩል “ፀጋአብ ሦስት ዓመት ውል አለው እንዲሁም ተመስገን አንድ ዓመት ቀሪ ውል አላቸው ወደየትም ክለብ መሄድ የለባቸውም።” በማለት ለፌዴሬሽኑ ደብዳቤ አስገብተው ነበር። ተጫዋቾቹም በበኩላቸው ምላሽ ሲሰጡ ፀጋአብ “እጄ ላይ ውሉ አለ ነፃ ተጫዋች በመሆኔ ወደ አሳዳጊዬ ክለብ ሄጃለው።” በማለት መከራከርያውን ሲያቀርብ ተመስገን በበኩሉ “ስድስት ዓመት ሀዲያን አገልግዬ ህጉን ተከትዬ ነው ወደ ቅዱስ ጊዮርጊስ የሄድኩት” በማለት ለሶከር ኢትዮጵያ ተናግረው ነበር።

ዛሬ የሁለቱንም አካላት ጉዳይ ሲከታተል የቆየው ፌዴሬሽኑ ባስተላለፈው ውሳኔ ሁለቱም ተጫዋቾች በቢጫ እና በአረንጓዴ ቲሴራ ግዴታቸውን ስለተወጡ የመልቀቅ ሙሉ መብት ያላቸው ስለሆኑ ወደ ፈለጉበት ክለብ ሄደው መጫወት እንደሚችሉ ውሳኔ ሰጥቷል።

ስለሆነም ሁለቱ ተጫዋቾች በይፋ የቅዱስ ጊዮርጊስ ተጫዋቾች መሆናቸው ሲረጋገጥ ነገ ዝውውራቸውን ፌዴሬሽን በመሄድ የሚያፀድቁ መሆኑን አውቀናል።