በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት በሽረ ምድረ ገነት ቆይታ የነበረው ተከላካይ ወደ አዲስ አዳጊው አመራ

በዝውውር መስኮቱ የበርከት ያሉ ነባር ተጫዋቾች ውል ያራዘሙት እና በዛሬው ዕለት የቀድሞ ተጫዋቻቸው ሽመክት ጉግሳን ለማስፈረም ከጫፍ የደረሱት ሀላባ ከተማዎች አሁን ደግሞ በተጠናቀቀው ዓመት በሽረ ምድረ ገነት ቆይታ የነበረው የመሀል ተከላካዩ ፀጋአብ ዮሐንስ ለማስፈረም ከስምምነት ደርሰዋል።
በተጠናቀቀው ዓመት በሀያ ስምንት ጨዋታዎች ተሳትፎ 2301 ደቂቃዎች ሜዳ ላይ የቆየው ፀጋአብ ዮሐንስ ከሀዋሳ ከተማ ታዳጊ ወደ ዋናው ቡድን አድጎ ለስድስት ዓመታት አሳዳጊ ክለቡን ማገልገሉ የሚታወስ ሲሆን አሁን ደግሞ ከአንድ ዓመት የሽረ ቆይታ በኋላ ወደ ሀላባ ከተማ ለማምራት ከስምምነት ደርሷል።

