በሽረ ምድረ ገነት ቆይታ የነበረው ተጫዋች ወደ ሌላው የሊጉ ክለብ ለማምራት ተቃርቧል

በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት በሽረ ምድረ ገነት ቆይታ የነበረው ሁለገቡ ሽመክት ጉግሳ በቀጣይ የውድድር ዓመት ተጠናክረው ለመቅረብ የነባር ተጫዋቾች ውል በማራዘም እና አዳዲስ ተጫዋቾች በማስፈረም ላይ ወደ የሚገኙት አዲስ አዳጊዎቹ ሀላባ ከተማዎች ለማምራት ከጫፍ ደርሷል።
በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት በሀያ ዘጠኝ ጨዋታዎች ተሰልፎ 2360 ደቂቃዎች ቡድኑን ያገለገለው ሽመክት በ2011 ደደቢትን ለቆ ወደ ዐፄዎቹ ቤት በማምራት ለስድስት ዓመታት ፋሲል ከነማን ማገልገል የቻለ ሲሆን ባለፉት ሁለት ዓመታት ደግሞ በኢትዮ ኤሌክትሪክ እና ሽረ ምድረ ገነት ቆይታ ማድረጉ ይታወሳል። ሁለገቡ ተጫዋች ከዚ ቀደም በኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ጨምሮ ወላይታ ድቻ፣ አየር ኃይል፣ ሀዋሳ ከተማ ፣ ደደቢት ፣ ኢትዮ ኤሌክትሪክ እና በሽረ ምድረ ገነት መጫወቱም ይታወሳል።

