መሳይ ተመስገን በይፋ የያንግ አፍሪካንስ ተጫዋች ሆናለች

መሳይ ተመስገን በይፋ የያንግ አፍሪካንስ ተጫዋች ሆናለች

ከሁለት ሳምንታት በፊት እንደነገርናችሁ የታንዛኒያው ክለብ ኢትዮጵያዊቷን አጥቂ ማስፈረሙን ይፋ አድርጓል።

ከሳምንታት በፊት የኢትዮጵያ ንግድ ባንኳ የአማካይ እና አጥቂ ቦታ ተሰላፊዋ መሳይ ተመስገን ለታንዛኒያው ክለብ ያንግ አፍሪካንስ ለመፈረም ጫፍ ላይ መድረሷን በይፋ አሳውቀናችሁ ነበር። ሆኖም ክለቡ ዛሬ ዝውውሩ መጠናቀቁን ይፋ አድርጓል።

መሻዋን ከወጣቶች ስፖርት አካዳሚ አድርጋ በኢትዮ ኤሌክትሪክ ፣ መቻል እና ንግድ ባንክ ቆይታ የነበራት አጥቂዋ በኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን በሁሉም የዕድሜ እርከኖች መጫወት የቻለችው መሳይ አሁን በያንግ አፍሪካንስ የምትቆይበትን የአንድ ዓመት ውል አስራለች።

በታንዛኒያ ያንግ አፍሪካንስ አረጋሽ ካልሳ ፣ በሲምባ ኩዊንስ ሴናፍ ዋቁማ እየተጫወቱ እንደሚገኙ የሚታወቅ ሲሆን ቀደም ብላ ወደ ሞሮኮው ቢርካን ክለብ ከተጓዘችውን አርያት ኦዶንግ እና አሁን በንግድ ባንክ ከምትገኘው ኝቦኝ የን ቀጥሎ መሳይ ተመስገን ወደ ታንዛኒያ ሊግ ያመራች አምስተኛ ወደ ያንግ አፍሪካንስ ያመራች ደግሞ አራተኛዋ ኢትዮጵያዊት ተጫዋች መሆን ችላለች።