የሉሲዎቹ አጥቂዎች ቡድኑን ተቀላቅለዋል

የሉሲዎቹ አጥቂዎች ቡድኑን ተቀላቅለዋል

ታንዛኒያ ሊግ የሚጫወቱት ኢትዮጵያውያን የሉሲዎቹን ስብስብ መቀላቀላቸው ታውቋል።

በ2028 የሎስ አንጀለስ ኦሊምፒክ የሴቶች እግር ኳስ ሁለተኛ ዙር ማጣሪያ ከ ሩዋንዳ ጋር መስከረም 27 እና ጥቅምት 3 ሁለት ጨዋታዎችን የሚያደርገው የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ልምምዱን አጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን ጥሪ ቀርቦላቸው እስካሁን ቡድኑን ያልተቀላቀሉት በታንዛኒያ ሊግ የሚጫወቱት የያንግ አፍሪካንሷ መሳይ ተመስገን እና የሲምባ ኩዊንሷ ሴናፍ ዋቁማ ዛሬ ቡድኑን መቀላቀላቸው ታውቋል።

ሁለቱም ተጫዋቾች በታንዛኒያ የሴቶች ሊግ ግሩም ግቦችን በማስቆጠር በተለይም ሴናፍ ዋቁማ ቡድኗን ቻምፒዮን በማድረግ ደማቅ አጀማመር እያደረጉ እንዳሉ ይታወቃል።