ሎዛ አበራ የሉሲዎቹን ስብስብ ለምን አልተቀላቀለችም?

ሎዛ አበራ የሉሲዎቹን ስብስብ ለምን አልተቀላቀለችም?

አንጋፋዋ አጥቂ ለሴቶች ብሔራዊ ቡድን ጥሪ ቢቀርብላትም ቡድኑን አልተቀላቀለችም።

በሎስ አንጀለስ አስተናጋጅነት ለሚካሄደው የ2028 ኦሊምፒክ የሴቶች እግር ኳስ ውድድር ማጣሪያ በአሰልጣኝ ቻለው ለሜቻ እየተመራ የሚቀርበው የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ዛሬ ለመጀመሪያው ጨዋታ ወደ ሩዋንዳ እንደሚያቀና የታወቀ ሲሆን ከሀገር ውጪ ለሚጫወቱ ተጫዋቾች በቀረበው ጥሪ መሠረት የሲምባዋ ሴናፍ ዋቁማ እና የያንግ አፍሪካዋ መሳይ ተመስገን በትናንትናው ዕለት ቡድኑን ሲቀላቀሉ ለአሜሪካው ዲሲ ፖወር የምትጫወተው ሎዛ አበራ ግን ቡድኑን እስካሁን አልተቀላቀለችም።

ሶከር ኢትዮጵያ እንዳገኘችው መረጃ ከሆነ ደግሞ አጥቂዋ ቡድኑን ያልተቀላቀለችው ክለቧ ቶሎ ባለመልቀቁ እና ረጅም ጉዞ አድርጎ መምጣቱ የሚፈጥርባትን የድካም ጫና ታሳቢ በማድረግ ያልመጣች ሲሆን ከነገ ወዲያ በሚደረገው የመጀመሪያ ጨዋታ እንደማትሳተፍ ሲረጋገጥ ድሬዳዋ ላይ ለሚካሄደው የመልስ ጨዋታም የመገኘት ዕድሏ እጅግ ጠባብ እንደሆነ አረጋግጠናል።