የዐፄዎቹ ረዳት አሰልጣኞች ታውቀዋል

የዐፄዎቹ ረዳት አሰልጣኞች ታውቀዋል

የአሰልጣኝ ዘማርያም ወልደጊዮርጊስ ረዳት አሰልጣኞች እነ ማን እንደሆኑ ታውቋል።

ቅድመ ውድድር ዝግጅታቸውን በአዳማ ከተማ የጀመሩት ፋሲል ከነማዎች አሰልጣኝ ዘማርያም በቀጣይ ዓመት አብረዋቸው የሚሰሩትን ረዳቶቻቸውን አሳውቀዋል።

ምክትል አሰልጣኝ በመሆን ኢንስትራክተር መብራቱ ሀብቱ ሲሾሙ ከዚህ ቀደም በባህር ዳር ከተማ ረጅም ጊዜ ምክትል አሰልጣኝ እንዲሁም የቪዲዮ ተንታኝ በመሆን ያገለግሉ ሲሆን በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የቪዲዮ ተንታኝ በመሆን ማገልገላቸው ሲታወቅ አሁን የአሰልጣኝ ዘማርያም ምክትል በመሆን የሚያገለግሉ ይሆናል።

የአካል ብቃት አሰልጣኝ በመሆን የተሾሙት ደግሞ ግርማይ ኪሮስ ሲሆኑ የፋሲል ከነማ ወጣት ቡድን አሰልጣኝ በመሆን ሲያገለግሉ የቆዩት ባለሙያው አሁን የአካል ብቃት አሰልጣኝ በመሆን መሾማቸው ታውቋል።