ነብሮቹ የተስፈኛውን ወጣት ውል አራዝመዋል

ነብሮቹ የተስፈኛውን ወጣት ውል አራዝመዋል

የግራ መስመር ተከላካዩ ባሳዳጊው ቤት ለተጨማሪ ዓመታት ለመቆየት ውሉን አራዝሟል።

ላለፉት ጥቂት ዓመታት በሀዲያ ሆሳዕና ቤት ከታዳጊ ቡድኑ ወደ ዋናው ቡድን ካደገበት ጊዜ ጀምሮ በሚያገኛቸው የጨዋታ ዕድሎች ተስፋ ሰጪ እንቅስቃሴ ሲያያደርግ የተመለከትነው የግራ መስመር ተከላካዩ ናትናኤል ሞገስ ውሉን ማራዘሙን ሰምተናል።

በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት በ20 ጨዋታዎች ላይ ተሳትፎ ያደረገው ናትናኤል ባሳዳጊው ቤት ለተጨማሪ ሁለት ዓመታት ለመቆየት መስማማቱን ክለቡ በላከልን መረጃ አውቀናል።