“ብሔራዊ ቡድኑ እንደ ክለብ ለአርባ ቀን ቅድመ ዝግጅት እያደረገ ነው።”

“ብሔራዊ ቡድኑ እንደ ክለብ ለአርባ ቀን ቅድመ ዝግጅት እያደረገ ነው።”

👉 “ሞሮኮ እንደ ቤታቸው ይመላለሱበታል በማለት ሲናገሩ እሰማለው…

👉 ወደ ሞሮኮ ለሽርሽር አንሄድም.. አቶ ኢሳያስ ጅራ

ያለፉትን ስምንት ዓመታት የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽንን በፕሬዝደንትነት የመሩት አቶ ኢሳያስ ጅራ በቀጣይ አራት ዓመት ዳግም እግርኳሱን ለመምራት ብቸኛ እጩ ተወዳዳሪ ሆነው መቅረባቸው ይታወቃል። በመሆኑም በቀጣይ ሊሰሩ ያሰቡትን በተመለከተ ለጋዜጠኞች ማብራሪያ እየሰጡ ሲገኝ። አብዛኛውን ከዚህ ቀደም የነበሩ የተዳጊዎች ልማት ፣ የአሰልጣኞች ስልጠና፣ ታዳጊ ፕሮጀክት ላይ፣ የዳኞች ልማት ላይ፣ የውድድሮች ልማትን እንዲሁም ከሌሎች አቻ ሀገራት ጋር ያለውን ግኑኝነት በማስመልከት አጠናክረው ለማስቀጠል ማሰባቸውን የገለፁ ሲሆን በተለየ ሁኔታ ከሞሮኮ ጋር ካለቸው ግኑኝነት በተመለከተ ሲናገሩ

አንዳንዶች ሞሮኮ እንደ ቤታቸው ይመላለሱበታል በማለት ሲናገሩ እሰማለው ሆኖም ግን ብሔራዊ ቡድናችን በሜዳው ማድረግ የሚገባውን ጨዋታ በመታገዱ ምክንያት ወደ ሞሮኮ በመሄዳችን ገልፀው በዚህም በዚህ አራት ዓመት ውስጥ የሞሮኮ እግርኳስ ፌዴሬሽን ከ80 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ እንዳደረጉላቸው ገልፀው ይህ ከፍተኛ ወጪ የቀነሰላቸው የስፖርት ዲፕሎማሲ ውጤት እንደሆነ እና ወደ ሞሮኮ ለሽርሽር እንደማይሄዱ ገልፀዋል።

አሁን ብሔራዊ ቡድናችን ወደ ሀገር ቤት ተመልሷል ለዚህ የባህርዳር ከተማ አመራሮችን በከፍተኛ ሁኔታ ላመሰገን ይገባል። እዚህ በመምጣታችን ትልቅ ለውጥ ነው። የሚቀሩን መሰረተ ልማቶች አሉ እርሱንም እንሰራበታለን። ካሉ በኋላ አያይዘው ከወጪ ጋር ተያይዞ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡደን እንደ ክለብ ለአርባ ቀን እየተዘጋጀ ነው። ይህ ከፍተኛ ወጪ እያስወጣቸው መሆኑን ተናግረዋል። ትውለደ ኢትዮጵያውያን በቅርብ ጌዜ አካተን ሀገርን የሚያኮራ ጠንካራ ብባሔራዊ ቡደን ለማምጣት ጥረት እንደሚያደርጉ አንስተዋል።