👉 “የሌለ ሀጥያት ለምን ለሰው እንሰጣለን”
👉 እኔ የማቀው ተወዳዳሪ መሆኔን ነው
👉 “በየትኛው ስልጣኔ ነው ደንብ ላሻሻሽል የምችለው
👉 “አንድ ግለሰብ እንዴት ደንብ ላሻሽል እችላለው፤ ብቻህን ለምን ተወዳደርክ ለተባልኩት …
አቶ ኢሳያስ ጅራ ጋዜጣዊ መግለጫ መስጠት ቀጥለዋል አስቀድመው መግቢያ ላይ ያነሷቸውን አንኳር አንኳር ነጥቦች ያቀረብን ሲሆን አሁን ደግሞ ብቸኛ ተወዳዳሪ መሆናቸውን አስመልክቶ ከጋዜጠኞች ለቀረበላቸው ጥያቄዎችን የሰጡት ምላሽ እነሆ !

ብቻዎትን መወዳደር አስፈላጊ ነው ? ይህ ለምን ሆን ?
“እኔ የማውቀው ተወዳዳሪ መሆኔን ነው፤ የውድድር ዶክሜንቴን ማስገባት ነው” በማለት በአጭሩ ከመለሱ በኋላ “ደንብ የማውጣት የማሻሻል ስልጣን ያለው ጠቅላለው ጉባኤው ነው። አንድ ግለሰብ እኔ እንዴት ደንብ ላሻሽል እችላለው። ጉባኤው ያፀደቀው ነው። የሌለ ሀጥያትን ለምን ለሰው እንሰጣለን። እናንተ እኔ ቦታ ብትሆኑ ታረጉታላቹሁ ብዙ ፌዴሬሽኖች ሦስት ተርም አድርገዋል ፊፋም እንደዛው ሦስት ተርም ነው አንድ ፕሬዝደንት መቀጠል የሚችለው። እንዴት እግርኳሱ ላይ ሲሆን ይህ ጥያቄ ይነሳል። በመሠረቱ ይህ ጉዳይ መታረም አለበት። በየትኛው ስልጣኔ ነው ደንብ ላሻሻሽል የምችለው ይህ መታረም አለበት ብለዋል።

