የዋልያዎቹ ዝግጅት ዛሬ ሲቀጥል ግብ ጠባቂው ከስብስቡ ጋር አይገኝም

በ2027 ለሚዘጋጀው የአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ የምድቡን የመጀመሪያ ሁለት ጨዋታዎችን ከሱዳን እንዲሁም ከሴኔጋል አቻዎቹ ጋር በጁባ እና በባህርዳር ከተማ የሚያደርገው በአሰልጣኝ ዮሐንስ ሳሕሌ የሚመራው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዛሬ በአደይ አበባ ስታድየም የሦስተኛ ሳምንት ልምምዱን እያከናወነ ይገኛል።
በዛሬው ዕለት እየተከናወነ በሚገኘው ልምምድም ላለፉት ሳምንታት ከቡድኑ ጋር ልምምድ በመስራት ላይ የሰነበተው ግብ ጠባቂው ሰይድ ሀብታሙ እንዳልተሳተፈ አይተናል። በዛሬው ልምምድ በስፍራው ተገኝታ የተከታተለችው ሶከር ኢትዮጵያ ግብ ጠባቂው በምን ምክንያት ከቡድኑ ጋር እንደማይገኝ ባደረገችው ማጣራትም ተጫዋቹ በግል ጉዳይ እንደሌለ እና በቀጣዮቹ ቀናት ተመልሶ ቡድኑን እንደሚቀላቀል ታውቋል።

