ሁለት ተጫዋቾች ከቡድኑ ተነጥለው ሲሰሩ ተመልክተናል

ሁለት ተጫዋቾች ከቡድኑ ተነጥለው ሲሰሩ ተመልክተናል

በዛሬው የዋልያዎቹ ልምምድ ሁለት ተጫዋቾች ከቡድኑ ተነጥለው ልምምድ ሰርተዋል

በአሰልጣኝ ዮሐንስ ሳሐሌ የሚመሩት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በአዲሱ ዓመት መስከረም ወር ለሚያደርጋቸው ሁለት የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የምድብ ጨዋታዎች ከሳምንታት በፊት የጀመሩትን ዝግጅት አጠናክረ ቀጥለዋል። ዋልያዎቹ ዛሬ ከ3:00 ሰዓት ጀምሮ በአደይ አበባ ስታድየም ልምምዳቸውን እየሰሩ ሲሆን ሁለት የብሔራዊ ቡድን ተጫዋቾች በጉዳት ምክንያት ከቡድኑ ተነጥለው ሲሰሩ ተመልክተናል።

ተጫዋቾቹ የቅዱስ ጊዮርጊሱ ፀጋአብ ግዛው እና የመቻሉ ግሩም ሐጎስ ሲሆኑ የጉዳታቸው መጠን ምን ያህል እንደሆነ ለጊዜው መረጃው ባይኖረንም ሁለቱም ከቡድኑ ተነጥለው በሜዳው መሮጫ መም ላይ መጠነኛ እንቅስቃሴ ሲያደርጉ እና
በህክምናው ባለሙያ ክትትል ሲደረግላቸው አስተውለናል።