ዋልያዎቹ እና ፈረሰኞቹ የአቋም መፈተሻ ጨዋታ ሊያደርጉ ነው

ዋልያዎቹ እና ፈረሰኞቹ የአቋም መፈተሻ ጨዋታ ሊያደርጉ ነው

ለአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ዝግጅቱን እያደረገ የሚገኘው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የአቋም መፈተሻ ጨዋታ ለማድረግ ቀጠሮ ይዟል

በ2027 ለሚዘጋጀው የአፍሪካ ዋንጫ ከሱዳን እና ከሴኔጋል አቻዎቹ ጋር በመስከረም ወር ለሚያደርጋቸው ሁለት የማጣሪያ ጨዋታዎች መቀመጫውን አዲስ አበባ በማድረግ ዝግጅት ከጀመረ ሦስት ሳምንታት የደፈነው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በአሰልጣኝ ሰርዲዮቪች ሚሊቱን ከሚመራው ቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር የአቋም መለክያ ጨዋታ ለማድረግ ቀጠሮ ይዟል።

እስካሁን የዝግጅቱ አካል ከሆነው የእርሰ በእርስ ጨዋታ በስተቀር የአቋም መለኪያ ጨዋታ ያላደረገው ብሔራዊ ቡድኑ ነገ ረፋድ በቢሸፍቱ ክብሩ ይድነቃቸው ተሰማ አካዳሚ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር የአቋም መለክያ ጨዋታ ለማድረግ ቀጠሮ መያዙን ሰምተናል።