ከምድረ ገነት ሽረ ጋር በግሉ ጥሩ ቆይታ የነበረው አቤል ማሙሽ ወደ ቀድሞ ክለቡ ለመመለስ ተስማምቷል

ከሞጆ የተገኘውና በ2015 የከፍተኛ ሊግ ውድድር ኮኮብ ጎል አስቆጣሪ ሆኖ ያጠናቀቀው እንዲሁም በ2016 ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር የፕሪምየር ሊግ ዋንጫን ያነሳው አጥቂው አቤል ማሙሽ ወደ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተመልሷል።
ባለፉት ሁለት ዓመታት በባህር ዳር ከተማ እና በሽረ ምድረ ገነት ቆይታ ያደረገው እና በተጠናቀቀው የውድድር ዘመን አምስት ጎሎችን በማስቆጠር በግሉ ጥሩ ዓመት ያሳለፈው አጥቂው አሁን ደግሞ ከሁለት ዓመታት በኋላ የሊጉን ዋንጫ ወደ አነሳበት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለመመለስ ከስምምነት ደርሷል።

