ሲዳማ ቡና ከኤግሎን የሚያደርገው የቻምፒዮንስ ሊግ የቅድመ ማጣሪያ የመልስ ጨዋታ የቀጥታ ሥርጭት ሽፋን ያገኛል።

በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ቻምፒዮን በመሆን ኢትዮጵያን በካፍ ቻምፒዮንስ ሊግ የወከለው ሲዳማ ቡና በቅደመ ማጣሪያው ከቻዱ ክለብ ኤጌሎን ጋር ተደልድሎ በመጀመሪያው ጨዋታ ያለ ግብ የተለያየ ሲሆን ዛሬ 10 ሰዓት ላይ የመልሱ ጨዋታ በድሬዳዋ ስታዲየም ይደረጋል።
ይህን ጨዋታም በሲዳማ ቡና ክለብ የፌስቡክ ገጽ በቀጥታ ሥርጭት እንደሚተላለፍ ሶከር ኢትዮጵያ አውቃለች።

