ወጣቱ ተከላካይ ወደ ወልዋሎ አመራ

ወጣቱ ተከላካይ ወደ ወልዋሎ አመራ

ባለፉት ዓመታት በመቐለ 70 እንደርታ ቆይታ የነበረው ተከላካይ ወደ ወልዋሎ አቅንቷል።

በካፍ ኮንፌዴሬሽን ካፕ የመጀመሪያ ዙር ማጣሪያ የሱዳኑ ሂላል አልሳሕን በመርታት ወደ ቀጣዩ ዙር የተሸጋገሩት ወልዋሎዎች ላለፉት ሦስት የውድድር ዓመታት መቐለ 70 እንደርታን ያገለገለው የመሀል ተከላካዩ ዘረሰናይ ብርሃነን አስፈርመዋል።

ከምዓም አናብስት ሁለተኛ ቡድን ተገኝቶ ላለፉት ዓመታት በእናት ክለቡ ቆይታ የነበረው ተጫዋቹ በ2016 በትግራይ እግር ኳስ ፌደሬሽን አዘጋጅነት በተካሄደው ክልል አቀፍ የአንበሳ ባንክ ውድድር ላይ ጥሩ ብቃት ካሳየ በኋላ ባለፉት ዓመታት በመቐለ 70 እንደርታ መለያ መጫወቱ የሚታወስ ሲሆን አሁን ደግሞ ወደ ወልዋሎ አምርቷል።