ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ስብስብ ውስጥ አንድ ተጫዋች ቡድኑን አለመቀላቀሉ አውቀናል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የ2027 የአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ በቀጣዩ ሳምንት በቀናት ልዩነት ለሚያደርገው ጨዋታ ዝግጅቱን ማድረጉን ሲቀጥል የቡድኑ አሠልጣኝም ዛሬ ፀጋአብ ግዛው ፣ ታምራት እያሱ እና አማኑኤል ተርፉን መቀነሳቸው አስቀድመን መረጃ አድርሰናችሁ ነበር።
አሁን ደግሞ የወልዋሎ ዓ/ዩ ተጫዋች ነፃነት ገብረመድን ቡድኑን አለመቀላቀሉን ሰምተናል። ተጫዋቹ ስለ መቀነሱ በግሉም ሆነ ለክለቡ እስካሁን የተላከ ደብዳቤ አለመኖሩን ታውቋል። ነፃነት ክለቡን አገልግሎ ዛሬ ማምሻውን ከድሬደዋ ተነስቶ አዲስ አበባ የገባ ሲሆን ወደ ሀዋሳ አቅንቶ ቡድኑን አለመቀላቀሉን አረጋግጠናል።
ሶከር ኢትዮጵያ በዚህ ጉዳይ ላይ የሚኖሩ መረጃዎችን አጣርታ የምትመለስ ቢሆንም ምን አልባት ተጫዋቹ ከብሔራዊ ቡድኑ ስብስብ ውጭ የመሆኑ ዕድል መስፋቱን የውስጥ ምንጮቻችን ነግረውናል። የምንጮቻችንን መረጃ የሚያጠናክረው ደግሞ ከወልዋሎ የተጠሩት አዳዲሶቹ ተጫዋቾች ዛሬ ሀዋሳ እንዲገቡ ጥሪ ሲቀርብ ለነፃነት ጥሪ አለመደረጉ ነው።

