ኢትዮጵያዊው አሠልጣኝ የዩጋንዳ ብሔራዊ ቡድን አሠልጣኝ ሆነ

ኢትዮጵያዊው አሠልጣኝ የዩጋንዳ ብሔራዊ ቡድን አሠልጣኝ ሆነ

ያለፉትን ሁለት አመታት በዩጋንዳ ያሳለፈው አሠልጣኝ የሀገሪቱ የሴቶች ብሔራዊ ቡድን አሠልጣኝ ሆኖ መሾሙ ይፋ ሆኗል።

በተለያዩ የእድሜ እርከን ቡድኖች የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድኖችን ያሰለጠነው አሠልጣኝ ፍሬው ከሁለት አመታት በፊት ከሀገር ወጥተው የዩጋንዳውን ካምፓላ ኩዊንስ ክለብ ማሰልጠን እንደጀመሩ ይታወሳል። አሠልጣኙ ከክለቡ ጋር የሊጉን እና የፉፋ ዋንጫን ካነሳ በኋላ ውሉ መጠናቀቁን ተከትሎ ከሳምንታት በፊት ከክለቡ ጋር መለያየቱ የሚታወስ ሲሆን አሁን የዩጋንዳ እግርኳስ ፌዴሬሽን ይፋ እንዳደረገው ከሆነ አሠልጣኙ የሀገሪቱ የሴቶች ብሔራዊ ቡድን አሠልጣኝ ሆኖ ተሹሟል።

አሠልጣኙ እስከ 2029 (እ.አ.አ) ድረስ ውል የፈረመ ሲሆን ከቀናት በኋላም የሀገሪቱ የኦሎምፒክ ብሔራዊ ቡድን ከዛምብያ ጋር ለሚያደርገው ጨዋታ ዝግጅቱን ከነገ አንስቶ እንደሚጀምር ተሰምቷል።