አራት ኢትዮጵያውያን ዳኞች በቀጣይ ሳምንት የሚደረገውን ከ23 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ የማጣርያ ጨዋታ ይመራሉ

በግብፅ አዘጋጅነት ለሚካሄደው ከ23 ዓመት በታች አፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ የሁለተኛ ዙር የመጀመሪያ ጨዋታዎች በቀጣይ ሳምንት መካሄድ ይጀምራሉ። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከሞሮኮ አቻው ጋር በድሬዳዋ ከተማ ከሚያከናውነው የመጀመርያ ጨዋታ በተጨማሪ ሀገራችን በአህጉራዊ ውድድሩ በአራት ኢትዮጵያውያን ዳኞች ትወከላለች።
ኢስዋቲኒ ከ አልጄሪያ ጋር በኢስዋቲኒ ዋና ከተማ ምባባኔ ረቡዕ ሕዳር 2 የመጀመርያው ጨዋታ የሚደረግ ይሆናል። ይህን ጨዋታን በመሐል ዳኝነት ኢንተርናሽናል ዋና ዳኛ ሃይማኖት አዳነ ሲመራ፤ ኢንተርናሽናል ረዳት ዳኞቹ ትግል ግዛው እና አማን ሞላ በረዳትነት፤ አራተኛ ዳኛ በመሆን ደግሞ ኢንተርናሽናል ዳኛ ማኑሄ ወልደፃድቅ በጋራ እንዲመሩት ታውቋል።

