ወሳኙን የሞዛምቢክ እና ኢትዮጵያ ጨዋታ ማን ይመራዋል?

ወሳኙን የሞዛምቢክ እና ኢትዮጵያ ጨዋታ ማን ይመራዋል?

የምድቡ አናት ላይ የምትገኘው ሞዛምቢክ እና የምድቡ ግርጌ ላይ የምትገኘው ኢትዮጵያ የሚያደርጉትን ወሳኝ ጨዋታ ምዕራብ አፍሪካዊ ዳኞች ይመሩታል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የ2027 የአፍሪካ ዋንጫ ላይ ለመሳተፍ በምድብ 10 ከሞዛምቢክ፣ ሴኔጋል እና ሱዳን ጋር ተደልድሎ እስካሁን የምድብ አንደኛ እና ሁለተኛ ጨዋታዎችን አከናውኖ ያለምንም ነጥብ የምድቡ አራተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጦ 3ኛ የምድብ ጨዋታውን ለማድረግ ወደ ሞዛምቢክ ማፑቶ አምርቷል። ከሁለት ጨዋታ አራት ነጥቦችን ይዞ በግብ ክፍያ በልጦ የምድቡ መሪ የሆነው የሞዛምቢክ ብሔራዊ ቡድን ሱዳንን በሜዳው 4ለ1 ካሸነፈ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ዋልያዎቹን ዓርብ ያስተናግዳል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ወደ አፍሪካ ዋንጫው ለማለፍ ወሳኝ የሆነውን ይህንን ጨዋታ ደግሞ የምዕራብ አፍሪካ ዜግነት ያላቸው አራት የቶጎ አልቢትሮች ጨዋታውን ይመሩታል።

ጨዋታውን በመሐል ዳኝነት አሪማ መሀመድ ሙስጠፋ አካፖ ከረዳቶቻቸው ጆናታን አሆንቶ ኮፊ እና ሚፍታሁ አሚዱ እንዲሁም አራተኛ ዳኛው አክሌሶ ንያማ ጋር እንዲመሩት ተመድበዋል።