ሎዛ አበራ በዲሲ ፓወር ታሪክ አዲስ ምዕራፍ ከፈተች

ሎዛ አበራ በዲሲ ፓወር ታሪክ አዲስ ምዕራፍ ከፈተች

አብዩ አረጋሽ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አምበል ሎዛ አበራ የአሜሪካው ዲሲ ፓወር የምንጊዜም ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ መሆን ችላለች

በአሜሪካ የሴቶች ዩ ኤስ ኤል ሱፐር ሊግ በሚወዳደረው ዲሲ ፓወር ተጫዋች የሆነችው ሎዛ አበራ በክለቡ ታሪክ ውስጥ ልዩ ስፍራ የሚያሰጣትን ታላቅ ስኬት ማስመዝገብ ችላለች።

ሎዛ ቡድኗ ከሌክሲንግተን ኤስሲ ጋር ባደረገው እና 2ለ1 ድል ባስመዘገበበት ፍልሚያ ቡድኗን ቀዳሚ ያደረገችውን ግብ በማስቆጠር በዲሲ ፓወር ታሪክ የከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነት ስፍራ ያዘች።

ይህ ስኬት ይበልጥ ልዩ የሚያደርገው ሎዛ ለክለቡ 60ኛ ጨዋታዋን ባደረገችበት ዕለት መሆኑ ነው። በዚህም ለዲሲ ፓወር ያስቆጠረቻቸውን ግቦች 17 በማድረስ የክለቡ የምንጊዜም ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ በመሆን ታቅ ስኬት አስመዝግባለች።