አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ በሞዛምቢክ ጨዋታ ዙርያ ምን አሉ ?

አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ በሞዛምቢክ ጨዋታ ዙርያ ምን አሉ ?


👉 “ከውድድሩ ላለመውጣት ነጥብ ይዘን ለመምጣት..

👉 “አሁን ትኩረቴ ጨዋታ ላይ ነው፤ ከውል ጋር የተያያዙ ነገሮች..

👉 “አንድ ተጫዋች ጎል ስላስቆጠረ ብቻ አይመረጥም..

👉 “የትኛውም ውጤት ይምጣ በእርግጠኝነት ያለቸውን ለመስጠት ዝግጁ ናቸው

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በ2027 የአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ከሞዛምቢክ ጋር በሚያከናውነው የምድብ 3ኛ እና 4ኛ ጨዋታዎችን ዙርያ ዋና አሰልጣኙ ዮሐንስ ሳህሌ በቡድኑ ወቅታዊ ዝግጅት እና ተያያዥ ጉዳዮች አስመልክቶ ለመገናኛ ብዙሃን ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል። በጋዜጣዊ መግለጫው የተነሱ አንኳር አንኳር ነጥቦችም እንደሚከተለው አቅርበነዋል።

አዳዲስ ተጫዋች የመምረጣቸው ምክንያት ?

ቡድኑ ውስጥ 13 አዲስ ተጫዋቾች ለመምረጥ የተገደድኩት በዋናናት በጉዳት ያልተጫወቱ በመኖራቸው፣ በቡድናቸው በቂ የጨዋታ ጊዜ ያላገኙ፤ ከብሔራዊ ቡድን ከወጡ በኋላ በጥሩ ብቃት ላይ ያልተገኙ በመኖራቸው እና ምንም ጨዋታ ያልተጫወቱ ተጫዋቾች ስላሉ አዳዲስ ተጫዋቾች ለመምረጥ ተገድጃለው ብለዋል።

የተጨዋቾች የጉዳት ሁኔታ?

” በረከት ሳሙኤል ከጉዳቱ አገግሞ ወደ ሙሉ ልምምድ መመለሱ አውቀናል። ቸርነት ጉግሳም ተነስቷል ደህና መሆኑን አሳይቷል። ለጨዋታው ዝግጁ ነው የሚለውን የህክምና ክፍሉ የሚወሰኑ ቢሆንም በቀሩት ቀናቶች የሚሆነውን እናያለን” በማለት ገልፀዋለወ።

ከሞዛምቢክ ጨዋታ ምን እንጠብቅ ?

ከውድድሩ ላለመውጣት ነጥብ ይዘን መምጣት ያስፈልጋል። ውድድሩ ውስጥ መቆየት ካለብን ማሸነፍ ካልሆነ ደግሞ ነጥብ ተጋርቶ መምጣት ዋና ዕቅዳቸው ነው። በእርግጠኝነት መናገር እችላለው ተጫዋቾች ያላቸውን ነገር ለመስጠት ዝግጁ ናቸው።

የመሳይ ሰለሞን አለመመረጥ ?

በወቅታዊ ብቃት ተጫዋቾች መርጠናል። ጎል በብዙ መንገድ ሊገባ ይችላል። የግድ በአጥቂ ብቻ ጎል አይቆጠርም። በዘመናዊ እግርኳስ በብዙ መንገድ ጎል ሊቆጠር ይችላል፤ ይሄን እየተመለከትን ነው። አንድ ተጫዋች ጎል ስላስቆጠረ ብቻ አይመረጥም። ሁሉንም መመርጥ አንችልም።

የአፍሪካ ዋንጫ ማሳለፍ ዋና ስምምነት ነው በሞዛምቢክ ውጤቱ ባይሳካ አትቀጥልም … ?

አሁን ትኩረቴ ጨዋታ ላይ ነው። ከውል ጋር የተያያዘ ነገሮች አሁን ምንም ማለት አልችልም።እርሱ የውል ጉዳይ ስለሆነ ጣጣ የለውም። አሁን ትኩረቴ ጨዋታው ላይ ብቻ ነው።