👉 “የነገው ጨዋታ ጠንካራ እና ከባድ ነው”
👉 “በሀገርህ ሲሆን ሦስት ነጥቡ ግዴታ ስለሚሆንብህ እያጠቃህ ነው የምትጫወተው”
👉 “ደጋፊዎች ማበረታታት ነው ያለባቸው እኛም ደግሞ ያው የአቅማችንን ለመስጠት ዝግጁ ነን”
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አምበል ጋቶች ፓኖም ከነገው የሞዛምቢክ ወሳኝ ጨዋታ በፊት የቅድመ ጨዋታ አስተያየት ሰጥቷል።

ከሞዛምቢክ ጋር በቻን ተገናኝተው ስላደረጉት ጨዋታ
ቻን ሀገር ውስጥ የሚጫወቱ ተጫዋቾች ብቻ የሚጫወቱበት ውድድር ነው። ይሄ ውድድር ግን ለየት ሚያደርገው ከአውሮፓም ከሌላም ክፍል ስለሚመጡ ይሄኛው ጠንከር ያለ ነው።
የሞዛምቢኩ ድል ለነገው ጨዋታ ላይ ስላለው ተፅዕኖ
ድሉ ከምደቡ ለማለፍ በውድድር እንድንቆይ አድርጎናል። ያንን ማሸነፋችን የራሳችንን ዕድል በራሳችን እንድንወስን አድርጓል። ስለዚህ የነገው ጨዋታ ጠንካራ እና ከባድ ነው። በሜዳችን እንደመጫወታችን ቢያንስ አድቫንቴጁ የእኛ ነው እና በልጆቹ ያለው ደሞ ያ ነው መንፈሱ አሪፍ ነው።
ከሦስት ቀናት በኋላ ስለሚደረገው ስለነገው ጨዋታ አቀራረብ
እንደ ተጫዋች ድካሙ ሁሉም ጋር ነው የሚሆነው። እንደ አጨዋወት ደሞ አሰልጣኝ ለሚሰጥህን ዝግጁ መሆን ነው ፤ ዋናው ታክቲክ ላይ ነው ትኩረት የምታደርገው የመከላከል ይሁን የማጥቃት ይሁን ልዩነት የለውም። ግን ይህንን አድርግ የተባለውን ማድረግ አይከበድም። ጨዋታ ውስጥ ያለ ነው። በሜዳ ስትጫወት የግድ ነጥብ ማግኘት ስላለብህ የማጥቃት አጨዋወት ነው የምትጫወተው ፤ ከሜዳ ውጭ ሲሆን ደግሞ ከሜዳ ውጪ መጀመሪያ ታያለህ ቲሞችን እያንዳንዱ ምድብ ላይ ነጥብ ያስፈልግሃል ለማለፍ ጥንቃቄ እያደረግክ መጫወት አለብህ ፤ በሀገርህ ሲሆን ሦስት ነጥቡ ግዴታ ስለሚሆንብህ እያጠቃህ ነው የምትጫወተው።
ነገ ከደጋፊው ስለሚጠበቅ ነገር እንዲሁም ደጋፊው ስለሚጠብቀው ነገር
ደጋፊዎች ማበረታታት ነው ያለባቸው እኛም ደግሞ ያው የአቅማችንን ለመስጠት ዝግጁ ነን። ቢያንስ ይሄን ዕድልም ለመጠቀም ሁሉም አእምሮ ላይ ያለው ነገር ዝግጁ እንደሆነ ነው። የአቅማችንን አድርገን ለመውጣት ነው የተዘጋጀነው።

