“ከጨዋታ መንገድ ጋር በተያያዘ ማፑቶ ላይ የተጠቀምነውን አጨዋወት ነው ነገም የምንደግመው”

“ከጨዋታ መንገድ ጋር በተያያዘ ማፑቶ ላይ የተጠቀምነውን አጨዋወት ነው ነገም የምንደግመው”

የሞዛምቢኩ አሠልጣኝ ቺኪንሆ ኮንዴ ከነገው ጨዋታ በፊት በባህር ዳር መግለጫ ሰጥተዋል።

ነገ 10 ሰዓት ከሚደረገው ወሳኝ የኢትዮጵያ እና ሞዛምቢክ ጨዋታ በፊት የምድቡ ሁለተኛ ደረጃ ላይ የምትገኘው ሞዛምቢክ አሠልጣኝ ቺኪንሆ ኮንዴ በባህርዳር ዳር ስታዲየም የቅድመ ጨዋታ መግለጫ ሰጥተዋል።

ስለቡድን ዜና

ከቡድኑ ጋር በተያያዘ ቡሩኖ ላንጋ ከጉዳት ጋር በተያያዘ በነገው ጨዋታ የመሰለፉ ነገር አጠራጣሪ ነው። ነገር ግን በዓርቡ ጨዋታ ያልነበረው ጊማ በነገው ጨዋታ ይኖራል። እርሱ ለቡድኑ በተለይ ለአማካይ መስመሩ ጥሩ ነገር ይሰጣል።

ስለአየር ሁኔታው

ከአየር ሁኔታው ጋር በተያያዘ የአየር ሁኔታው የተወሰነ የተጫዋቾቻችን ብቃት ላይ ተፅዕኖ እንደሚፈጥር እናስባለን። ነገርግን ተጫዋቾቻችን በብልጠት ጨዋታውን በምን አይነት መንገድ ማቀዝቀዝ እንዳለባቸው ያውቃሉ።

ምድቡ ላይ ስላለው ፉክክር

አሁን ላይ ኢትዮጵያ ቀጥተኛ የነጥብ ተቀናቃኛችን ናት። ሴኔጋል የምድቡ መሪ ስለሆነች አሁን በተለይ በሞዛምቢክ እና በኢትዮጵያ መካከል ነው ውይይቱ። እርግጥ ሱዳንም ሳትረሳ።

ወደኢትዮጵያ ስላደረጉት ጉዞ

ጉዟችን ጥሩ ነበር። እርግጥ የተወሰኑ ችግሮች ነበሩ በጉዞዋችን ዙሪያ ፤ ጠዋትም ረዘም ያለ ጊዜ በአዲስ አበባ ኤርፖርት አሳልፈናል። ነገር ግን በአጠቃላይ ጥሩ ጉዞ ነበር።

ስለነገው ጨዋታ አቀራረብ

ከጨዋታ መንገድ ጋር በተያያዘ ማፑቶ ላይ የተጠቀምነውን አጨዋወት ነው ነገም የምንደግመው። ከዚህ ቡድን ጋር ያለፉትን አምስት አመታት በደንብ ሰርተናል። ይሄ ቡድን ሞዛምቢክን ለቻን እና ለአፍሪካ ዋንጫ ያበቃ ነው። ስራው በወጥነት ሲሰራ የነበረ ነው። እርግጥ አሁን ላይ ሦስት ወሳኝ ተጫዋቾችን አጥተናል ከብሔራዊ ቡድን ራሳቸውን ስላገለሉ። ነገር ግን አሁን ላይ ቡድኑን በአዳዲስ ተጫዋቾች እያደራጀ ጥሩ ስራ እየተሰራ ነው።