ሀዋሳ ከተማ 1-1 ቅዱስ ጊዮርጊስ | የአሰልጣኞች አስተያየት

ውበቱ አባተ – ሀዋሳ ከተማ

ስለ ጨዋታው

“የመጀመሪያው አጋማሽ እና ሁለተኛው አጋማሽ እጅግ የተለየ መልክ ነበራቸው፡፡ የመጀመሪያውን 45 እኛ ከነሱ የተሻልን ነበርን ፣ ጥሩ ተጫውተን ግብ አስቆጥረናል፡፡ በሁለተኛው አጋማሽ እነሱ ግብ ስለተቆጠረባቸው ጥረት አድርገዋል ፤ ግብም አስቆጥረዋል፡፡ እኛ የመከላከል ሂደታችን ደካማ ነበር፡፡ ያገኘናቸውን እድሎች አስቆጥረን ጨዋታውን መጨረስ የምንችለው ጨዋታ ነበር፡፡”

“ያለፉት ጨዋታዎቻችን ጥሩ ስላልነበሩ ማሸነፍ እንፈልግ ነበር፡፡ ማጥቃት ላይ ብዙ ስለምንቆይ የኃላችንን እንዳናይ አድርጎናል፡፡ ዛሬ ከጉዳት በመጠኑም ቢሆን ተጫዋቾቼን አግኝቻለው ፤ ከታች ያደጉትም ደስ በሚል ሁኔታ ሲጫወቱ ነበር፡፡ ”

ቀጣይነት

” ቀጣይ ጨዋታዎችን አሸንፈን ከስጋት እንወጣለን፡፡ እኛን ዋጋ የሚያስከፍለን ያገኘናቸውን እድሎችበአግባቡ ባለመጠቀማችን ነው፡፡ ”

ስለ ቡድናቸው

” እኔ አስደሳች ቡድን በመስራቴ ደስተኛ ነኝ፡፡ በወጣቶቹም ተጫዋቾች እንቅስቃሴ እንደዛው፡፡ ”

ማርት ኑይ – ቅዱስ ጊዮርጊስ

ስለ ጨዋታው

” ጨዋታው ጥሩ አልነበረም ፤ ባይሆን ከባድ ጨዋታ ነበር፡፡ ጋዲሳ መብራቴ ተጫዋቾቼን ሲረብሽ ነበር፡፡ እንደ ቡድንም ሀዋሳዎች ጥሩ ነበሩ፡፡ እኛም በሁለተኛው አጋማሽ  ጥሩ ብንንቀሳቀስም አጋጣሚዎችን መጠቀም አልቻልም፡፡ ሜዳውም በእንቅስቃሴያችን ላይ ጫና አድርጎብናል፡፡ በአጠቃላይ  ጨዋታው ጥሩ አልነበረም ”

ስለ ተቃውሞው

“አሸንፈን መሪ ለመሆን ነበር ያሰብነው፡፡ እንቅስቃሴያችንም ጥሩ ነበር፡፡ ደጋፊዎቻችን ያነሱት ተቃውሞ ስራዬን እንድሰራ ያበረታታኛል፡፡ “

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *