ደደቢት 0-0 መከላከያ | የአሰልጣኞች አስተያየት 

አስራት ኃይሌ – መከላከያ

ስለ ጨዋታው

” በዛሬው ጨዋታ ላይ ቡድኔ ጥሩ አልነበረም ፤ በአጠቃላይ እንቅስቃሴያችን አሳማኝ አልነበረም፡፡ በዛሬው ጨዋታ ላይ እንዳሳየነው እንቅስቃሴ ከሆነ መሸነፍ ይገባን ነበር፡፡ ሁሉም ቦታዎች ላይ እርማቶች አድርገን ነበር ጨዋታውን የጀመርነው፡፡ ነገር ግን ልጆቼ ለውጤቱ ጎጉተው ይሆን አላውቅም የነገርኳቸውን ነገር የመዘንጋት ነገር ይታይ ነበር፡፡ ዞሮ ዞሮ ግን በጨዋታው ሙሉ ለሙሉ ተበልጠን ነበር፡፡”

ቀጣይ እቅድ

“አሁንም ቡድናችን ላይ ችግሮች አሉብን፡፡ ምክንያቱም በማጥቃት ላይ ያለን እንቅስቃሴ ጥሩ አይደለም ፣ የአጥቂዎቻችን የመዋለል ነገር ላይ ችግር ይታያል ፣ አማካይ መስመራችን ላይ ደግም ያለቀ ኳስ የሚያቀብል ተጫዋች የለም፡፡ ስለዚህ እነዚህን ነገሮች በቀጣይ ለማረም እንሰራለን፡፡ አሁንም ለሻምፒዮንነት ከሚጫወቱት ቡድኖች ብዙም አራቅንም፡፡ በቀጣይ ክፍተት ባሉብን ቦታዎች ላይ ተጫዋቾችን እየተመለከትን እንገኛለን በቀጣይ ያለብንን የቡድን ጥልቀት ጥበት በመቅረፍ ከመሪዎቹ ጋር ያለንን ልዩነት ለማጥበብ እንሰራለን፡፡”

ሻለቃ በለጠ ገብረኪዳን – መከላከያ

ስለ ጨዋታው

” ጥሩ ጨዋታ ነበር ፤ በሁለቱም ቡድኖች ጥሩ ፉክክር ተደርጓል ሆኖም ግን በተለይ በመጀመሪያው አጋማሽ ያገኘናቸው የግብ እድሎችን ባለመጠቀማችን አቻ ልንወጣ ችለናል እንጂ ማሸነፍ ይገባን ነበር፡፡”

ስለ ቡድኑ አቋም

“ከባለፈው የአርባምንጩ ጨዋታ በስተቀር በተከታታይ ጨዋታዎችን ማሸነፍ ችለናል፡፡ እንዲያውም በሊጉ ቢሸነፍም ቢያሸንፍም ግብ የሚያስቆጥረው ቡድን የኛ ነው፡፡ ወጥ የሆነ አቋም በማሳየት በኩል ችግር የለብንም፡፡”

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *