የአልጄርያ ብሄራዊ ቡድን በአዲስ ማልያ ኢትዮጵያን ይገጥማል

በአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ምድብ 10 አልጄርያ ከኢትዮጵያ ጋር ለምታደርጋቸው ተከታታይ ጨዋታዎች ግዙፉ የትጥቅ አምራች ኩባንያ አዲዳስ የተሰራውን አዲስ መለያ ለብሰው ይገባሉ፡፡

“ለ ፌኔስ” ከፑማ ጋር የነበራቸውን ውል በመጨረስ ከሌላው የጀርመን ትጥቅ አምራች ጋር በቅርቡ ውል የተፈራረመች ሲሆን በቶተንሃም ሆትስፐሩ ናቢል ቤንታሌብ አማካኝነት በዚህ ሳምንት ተዋውቋል፡፡ በሌሎች የቡድኑ ከዋክብት አማካኝነትም ማስታወቂያ ተሰርቶለታል፡፡

ትላንት ጠዋት በሁለቱ ብሄራዊ ቡድኖች መካከል በተደረገው ቅድመ ጨዋታ ስብሰባ የአልጄርያ ብሄራዊ ቡድን ነጩን ማልያ የሚለብስ ሲሆን ኢትዮጵያ ቢጫውን ማልያ ትጠቀማለች፡፡

PicsArt_1458900702397 teaser-pour-le-nouveau-maillot-de-lequipe-nationale

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *