አልጄርያ 7-1 ኢትዮጵያ
23’48’ ሶፊያን ፌጉይሊ
31’90+3 ኢስላም ስሊማኒ
72′ ያቺን ብራሂሚ
75′ ሳፊር ታይደር
80′ ራሺድ ጋዛል
——
85′ ጌታነህ ከበደ
ቀጥታ የፅሁፍ ስርጭት ከሶከር ኢትዮጵያ
ተጠናቀቀ!!!
ጨዋታው በአልጄርያ 7-1 አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡
ጎልልል!!!
90+3 ኢስላም ስሊማኒ ከመስመር የተሻገረለትን ኳስ ወደ ግብነት ቀይሮታል፡፡
*አልጄርያዎች ከየትኛውም አቅጣጫ የግብ ሙከራ በማድረግ ላይ ይገኛሉ፡፡ ከደርዘን በላይ ሙከራዎች አድርገው 6 ግብ አስቆጥረዋል፡፡
90′ መደበኛው ክፍለ ጊዜ ተጠናቆ 3 ደቂቃ ተጨምሯል፡፡
ጎልልል!!!! ኢትዮጵያ
85′ ጌታነህ ከበደ ከተከላካዮች ሾልኮ በመውጣት በሬይስ እግሮች መሃል አሾልኮ ለኢትዮጵያ የመጀመርያውን ግብ አስቆጥሯል፡፡
80′ ጎልልል!!!
ተቀይሮ የገባው ራሺድ ጋዛል ጎል አስቆጥሯል፡፡
*ማህሬዝ ተቀይሮ ወጥቷል፡፡ የሌስተሩ ኮከብ ከ5 ግቦች ሶስቱን አመቻችቶ አቀብሏል፡፡
75′ ጎልልል!!!! አልጄርያ
ሳፊር ታይደር ከማዕዘን ምት የተሻገረውን ኳስ እጅግ እጅግ እጅግ በግሩም ሁኔታ በቀጥታ መትቶ አስቆጥሯል፡፡
72′ ጎልልል!!!! አልጄርያ
ያቺን ብራሂሚ በመጨረሻም በግሩም ሁኔታ ግብ አስቆጥሯል፡፡
70′ ኢትዮጵያ ያለፉትን 10 ደቂቃዎች በአንፃራዊነት የተሻለ እንቅስቃሴ ማድረግ ችላለች፡፡
68′ ብራሂሚ ያሬድ ባዬን አታሎ በማለፍ ከታሪክ ጋር አንድ ለአንድ ቢገናኝም የመታውን ኳስ ታሪክ አውጥቶበታል፡፡
የተጫዋች ለውጥ – አልጄርያ
66′ ሪያድ ቦድቦውዝ ሁለት ግብ ያስቆጠረው ፌጉይሊን ቀይሮ ገብቷል፡፡
60′ ኢትዮጵያ እጅግ መጥፎ አቋም በማሳየት ላይ ትገኛለች፡፡ ቅብብሎቻችንም ቶሎ ቶሎ የሚቋረጡ ናቸው፡፡ በ60 ደቂቃዎች ውስጥ ቦሃኒ ሬይስን የሚፈትን ኢላማውን የጠበቀ ሙከራም ማድረግ አልቻልንም፡፡
55′ ታይደር ከርቀት የመታውን ኳስ ታሪክ በአግባቡ መቆጣጠር ሳይችል ቀርቷል፡፡ በቅርብ ርቀት የአልጄርያ ተጫዋች ቢኖር አጀገኛ ኳስ ነበር፡፡
53′ ብራሂሚ ከመስመር የተሻገረለትን ኳስ ሞክሮ አስቻለው ጨርፎ አውጥቶበታል፡፡ የተሻማውን የማዕዘን ምት ፌጉይሊ በአክሮባቲክ ምት ሞክሮ ወደ ውጪ ወጥቶበታል፡፡
51′ ማህሬዝ ከቅጣት ምት በቀጥታ የመታውን ኳስ ታሪክ መልሶታል፡፡
50′ ማህሬዝ የሞከረውን ኳስ ታሪክ ጌትነት እንደምንም አውጥቶታል፡፡
48′ ጎልልል!!! አልጄርያ
ሶፊያኔ ፌጉይሊ የቡድኑን 3ኛ ግብ አስቆጥሯል
ተጀመረ!
ሁለተኛው አጋማሽ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ተጀምሯል፡፡
የእረፍት ሰአት ቅያሪ
ዳዊት ፍቃዱ ገብቶ በሃይሉ አሰፋ ገብቷል፡፡
– – – –
የመጀመርያው አጋማሽ በአልጄርያውያን ሙሉ የበላይነት ተጠናቋል፡፡ የኢትዮጵያ እንቅስቃሴ ደግሞ አላማ የሌለው እና እርጋታ የማይታይበት ሆኗል፡፡
– – – – –
እረፍት!!!
የመጀመርያው አጋማሽ በአልጄርያ 2-0 መሪነት ተጠናቋል፡፡
45′ ስሊማኒ የሞከረው ኳስ በተከላካይ ተጨርፎ ወጥቷል፡፡
44′ ኢስላም ስሊማኒ ከመስመር የተሻገረለትን ኳስ በግንባሩ ገጭቶ ታሪክ አድኖበታል፡፡
44′ ቢጫ ካርድ
ኢስላም ስሊማኒ ፊሽካ ከተነፋ በኋላ ኳስ አላግባብ በማባከኑ የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል፡፡
41′ ጌታነህ ያሻገረለትን ኳስ ሽመልስ ወደ ግብ ሞክሮ በተከላካይ ተጨርፎ ወጥቶበታል፡፡ ይህ ለኢትዮጵያ የመጀመርያው የግብ ሙከራ ነው፡፡
38′ ያሬድ እና አስቻለው ስራ የበዛበት ምሽት እያሳለፉ ይገኛሉ፡፡ ከአልጄርያ ለሚሰነዘረው ተደጋጋሚ ጥቃት ሽፋን የሚሰጥ ተጫዋች ማግኘትም አልቻሉም፡፡
35′ ብራሂሚ የፍፁም ቅጣት ምቱን ሳይጠቀምበት ቀርቷል፡፡
34′ አሉላ ግርማ ኢስላም ስሊማኒን ጎትቶ በመጣሊሉ የፍጹም ቅጣት ምት ለአልጄርያ ተሰጥቷል፡፡
31′ ጎልልል!!! አልጄርያ
ኢስላም ስሊማኒ በመልሶ ማጥቃት ከማህሬዝ የተሻገረለትን ኳስ በቀላሉ ወደ ግብነት ቀይሮታል፡፡
28′ ፋውዚ ጉላም የመታውን ቅጣት ምት ታሪክ ጌትነት በቀላሉ መቆጣጠር አቅቶት ወደ ውጪ ወጥቶበታል፡፡
ጎልልል! አልጄርያ
23′ ሶፊያን ፌጉይሊ የመታው ኳስ በያሬድ ባየህ ተጨርፎ ግብ ሆኗል፡፡
20′ የኢትዮጵያ ተጫዋቾች ከራሳቸው የሜዳ ክልል መውጣት አልቻሉም፡፡ በብቸኛ አጥቂነት የተሰለፈው ጌታነህ ከቡድኑ ተነጥሏል፡፡
15′ አልጄርያ በኳስ ቁጥጥር ረገድ የበላይነት ብትወስድም ኢላማውን የጠበቀ የግብ ሙከራ ማድረግ አልቻለችም፡፡ ኢትዮጵያ በበኩሏ አመዛኙን ተጫዋች ከኳስ ጀርባ በማድረግ እየተንቀሳቀሰች ትገኛለች፡፡
8′ ማህሬዝ ከቀኝ መስመር ያሻማውን ቅጣት ምት አስቻለው ታመነ ከግብ አርቆታል፡፡
6’ፋውዚ ጉላም ከርቀት የሞከረው ኳስ ኢላማውን ስቶ ወጥቷል፡፡
5′ የኢትዮጵያ ተጫዋቾች በራሳቸው የግብ ክልል ኳስ እየተቀባበሉ ይገኛል፡፡ ይህም አልጄርያዎች በኢትዮጵያ የተከላካይ መስመር ላይ ጫና እንዲፈጥሩ አድርጓቸዋል፡፡
1’ተጀመረ
ጨዋታው በአልጄርያ ጀማሪነት ተጀምሯል
፡፡ ኢትዮጵያ ከቀኝ ወደ ግራ ፣ አልጄርያ ከግራ ወደ ቀኝ ያጠቃሉ፡፡
04:29 የሁለቱ ብሄራዊ ቡድን ተጫዋቾች ሰላምታ እየተለዋወጡ ይገኛሉ፡፡
04:27 በአሁኑ ሰአት የሁለቱ ሃገራት ብሄራዊ መዝሙር እየተዘመረ ይገኛል፡፡
3:30 ላይ የነበረው የስታድየሙ ድባብ
ፎቶ – Walid Byilka
የአልጄርያ አሰላለፍ (4-2-3-1)
1. ራሂስ ምቦልሂ
18. ሜህዲ ዜፋኔ – 2. አይሳ ማንዲ – 5. ሂቻም ቤልካውሪ – 3. ፋውዚ ጉላም
12. ካርል ሜጃኒ – 8. ሳፊር ታይደር
10. ሶፊያን ፌጉይሊ – 7. ሪያድ ማህሬዝ
– 11. ያሲን ብራሂሚ
13. ኢስላም ስሊማኒ
– – – –
የኢትዮጵያ አሰላለፍ (4-2-3-1/4-5-1)
22.ታሪክ ጌትነት
6.አሉላ ግርማ – 15.አስቻለው ታመነ – 3.ያሬድ ባዬ – 2.ተካልኝ ደጀኔ
7.ጋቶች ፓኖም – 8.አስራት መገርሳ
9.ራምኬል ሎክ – 18.ሽመልስ በቀለ – 14.በሀይሉ አሰፋ
9.ጌታነህ ከበደ
ተጠባባቂዎች
አቤል ማሞ ፣ አብዱልከሪም መሀመድ ፣ ሱሌይማን መሀመድ ፣ አንተነህ ተስፋዬ ፣ ታደለ መንገሻ ፣ ኤልያስ ማሞ ፣ ዳዊት ፍቃዱ