መከላከያ ከ ደደቢት – ቀጥታ የፅሁፍ ስርጭት

መከላከያ 0-0 ደደቢት

ተጠናቀቀ!!!
ጨዋታው ካለግብ ተጠናቋል፡፡

90+2′ ስዩም ከርቀት የመታው ኳስ ኢላማውን ስቶ ወጥቷል፡፡

90′ መደበኛው የጨዋታ ክፍለጊዜ ተጠናቆ 3 ደቂቃ ተጨምሯል፡፡

የተጫዋች ለውጥ – ደደቢት
88′
ተስሎች ሳይመን ወጥቶ ሚኪያስ ጸጋዬ ገብቷል፡፡

87′ ሳሙኤል ሳሊሶ እጅግ ለማመን በሚከብድ መልኩ ግልጽ የግብ ማስቆጠር አጋጣሚ አምክኗል፡፡

83′ ጆሴፍ አግዮኪ ከግብ ክልሉ አቅራቢያ የሞከረውን ኳስ ጀማል በቀላሉ ይዞታል፡፡

የተጫዋች ለውጥ – ደደቢት
83′
ያሬድ ብርሃኑ ወጥቶ ጆሴፍ አግዮኪ ገብቷል፡፡

79′ ሽመክት ከመስመር ያሻገረውን ኳስ ሳኑሚ በጭንቅላቱ ገጭቶ ጀማል ጣሰው ይዞበታል፡፡

የተጫዋች ለውጥ – መከላከያ
67′
ካርሎስ ዳምጠው ወጥቶ ማራኪ ወርቁ ገብቷል፡፡

ቢጫ ካርድ
61′
ሚልዮን በየነ በሽመክት ላይ በሰራው ጥፋት የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል፡፡

55′ ጨዋታው ከመጀመርያው አጋማሽ የተለደ እንቅስቃሴ እየታየበት አይደለም፡፡

ተጀመረ!!!!
ሁለተኛው አጋማሽ የጨዋታ ክፍለጊዜ ተጀመረ

– – – – – – – – – –
እረፍት!!!!
የመጀመርያው አጋማሽ እጅግ አሰልቺ በሆነ እንቅስቃሴ ታጅቦ ካለ ግብ ተጠናቋል፡፡

44′ ፍሬው ከመስመር ያሻገረውን ኳስ ሳሙኤል ሳሊሶ ሞክሮ ለጥቂት ወደ ውጪ ወጥቷል፡፡

ቢጫ ካርድ
36′
ሳሙኤል ሳሊሶ የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል፡፡

30′ ሳምሶን ጥላሁን ከርቀት የመታው ኳስ ኢላማውን ስቷል፡፡

ቢጫ ካርድ
21′
አክሊሉ አየነው ሳሙኤል ታዬ ላይ በሰራው ጥፋት የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል፡፡

20′ ጨዋታው እጅግ የተቀዛቀዘ እንቅስቃሴ እየተደረገበት ነው፡፡

10′ ከማዕዘን ምት የተሻማውን ኳስ ሳኑሚ ሞክሮ ወደ ላይ ወጥቶበታል፡፡

1′ የመከላከያ ተከላካዮችን ስህተት ተጠቆሞ ብርሃኑ ቦጋለ የሞከረው ኳስ በግቡ አናት ወደ ላይ ወጥቷል፡፡

ተጀመረ
ጨዋታው በመከላከያ አማካኝነት ተጀምሯል፡፡

የመከላከያ አሰላለፍ
1 ጀማል ጣሰው
29 ሙሉቀን ደሳለኝ – 16 አዲሱ ተስፋዬ – 20 ሚልዮን በየነ – 3 ቴዎድሮስ በቀለ
13 ሚካኤል ደስታ- 15 ቴዎድሮስ ታፈሰ – 19 ሳሙኤል ታዬ
10 ፍሬው ሰለሞን – 11 ካርሎስ ዳምጠው – 9 ሳሙኤል ሳሊሶ

ተጠባባቂዎች
22 ይድነቃቸው ኪዳኔ
2 ሽመልስ ተገኝ
26 ኡጉታ ኦዶክ
23 ሙጃሂድ መሃመድ
24 ቴዎድሮስ ግርማ
28 አቤል ከበደ
7 ማራኪ ወርቁ

የደደቢት አሰላለፍ
30 ብርሃኔ ፍስሃዬ
7 ስዩም ተስፋዬ – 14 አክሊሉ አየነው – 5 አይናለም ሃይለ – 2 ተካልኝ ደጀኔ
19 ሽመክት ጉግሳ – 24 ተስሎች ሳይመን – 8 ሳምሶን ጥላሁን – 10 ብርሃኑ ቦጋለ
99 ያሬድ ብርሃኑ – 11 ሳሙኤል ሳኑሚ

ተጠባባቂዎች
22 ታሪክ ጌትነት
29 ምኞት ደበበ
90 ሚኪያስ ፀጋዬ
27 አለምአንተ ካሳ
15 ጆን ቱፎር
28 ጆሴፍ አግዮ
32 ክዌሲ ኬሊ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *