ካርሎስ ዳምጠው ወደ ቢጫዎቹ አምርቷል

ካርሎስ ዳምጠው ወደ ቢጫዎቹ አምርቷል

ከወላይታ ድቻ ጋር ያለፉትን ዓመታት ቆይታ የነበረው አጥቂ ወደ ሌላ ክለብ ለማምራት ተስማምቷል።

በነገሌ አርሲ፣ በመቻል፣ በድሬዳዋ ከተማ፣ በኢትዮ ኤሌክትሪክ በለገጣፎ ለገዳዲ እና በወላይታ ድቻ ቆይታ የነበረው ካርሎስ ዳምጠው አሁን መዳረሻው ወልዋሎ ዓዲግራት ሆኗል።

በዝውውሩ የነቃ ተሳትፎ እያደረጉ ያሉት በአሰልጣኝ ግርማ ታደሰ የሚመሩት ወልዋሎዎች በአፍሪካ መድረክ እና በሀገር ውስጥ ለሚጠብቃቸው ውድድር ወደ ዝውውሩ በመግባት ጠንከር ያሉ ሥራዎችን እየሰሩ ይገኛሉ።