ኢትዮጵያዊቷ ኮከብ የምትገኝበት ክለብ ታውቋል

ኢትዮጵያዊቷ ኮከብ የምትገኝበት ክለብ ታውቋል

ለንግስት በቀለ የሙከራ ጊዜ የሰጠው የፈረንሳይ ክለብ ማነው ?

ቀደም ብለን የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን አጥቂ የሆነችው ንግስት በቀለ በአውሮፓው ክለብ እንደምትገኝ መግለፃችን ይታወሳል። የፊት መስመር ተጫዋቿ የሙከራ ዕድል የሰጣት ክለብም የፈረንሳዩ ሜትዝ መሆኑ ታውቋል። በአሁኑ ወቅት በሁለተኛው የሊግ እርከን በመሳተፍ ላይ የሚገኘው እና በ1974 በሜትዝ የተመሰረተው ክለቡ ባለፈው የውድድር ዓመት 12ኛ ደረጃን በመያዝ ያጠናቀቀ ሲሆን የሴቶች እግር ኳስ ከፍተኛ ትኩረት በሚሰጥበት ፈረንሳይ ውስጥ የሚገኝ አንጋፋ ክለብ ነው።

በኢትዮጵያ የሴቶች ብሔራዊ ቡድን ውስጥ በሁሉም የዕድሜ ክልሎች ያገለገለችው እንዲሁም በወጣቶች ስፖርት አካዳሚ፣ በቦሌ ክፍለ ከተማ፣ በመቻል እና በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተጫወተችው ንግስት በቀለ በስምንት ቀናት የሙከራ ቆይታ የተሳካ ጊዜ በማሳለፍ ላይ ስትገኝ የሙከራ ዕድሉ ተሳክቶላት በቋሚነት ከፈረመች በማልታው ቢርኪርካራ ከተጫወተችው ሎዛ አበራ ቀጥሎ በአውሮፓ የተጫወተች ኢትዮጵያዊት ትሆናለች።