የሊጉ ክስተት ነጌሌ አርሲ ለቀጣይ ዓመት ራሱን ለማጠናከር የመጀመርያ ፈራሚውን አግኝቷል።

የአሰልጣኝ ቱሉ ደስታን ውል በማራዘም የወሳኝ ተጫዋቾቻቸውን ርኆቦት ስላሎ፣ ዳዊት ተፈራ እና አለኝታ ማርቆስን ውል ያራዘሙት ነገሌዎች የመጀመርያ ፈራሚያቸውን መሐመድ ኑር ናስር ለማድረግ ተስማምተዋል።
በኢትዮጵያ መድን ፣ በጅማ ከተማ ፣ በኢትዮጵያ ቡና እና በተጠናቀቀው የውድድር ዘመን በድሬዳዋ ከተማ ያሳለፈው መሐመድኑር ናስር ሰጎኖቹን ለመቀላቀቀል የተስማማ የመጀመርያው ፈራሚ ሆኗል።

