ያሬድ ብሩክ ማረፊያው ታውቋል

ያሬድ ብሩክ ማረፊያው ታውቋል

በቅርብ ዓመታት በሊጉ ካየናቸው ባለተሰጥኦ አማካዮች መካከል አንዱ የሆነው ያሬድ ብሩክ ወደ ሌላ ክለብ አምርቷል።

በሀዋሳ ከተማ ከታዳጊ ወደ ዋናው ቡድን አድጎ በጥቂት ዓመታት ውስጥ በፕሪሚየር ሊጉ ከታዩ ባለተሰጥኦ አማካዮች አንዱ መሆን የቻለው ወጣቱ አማካዩ ያሬድ ብሩክ ወደ ነገሌ አርሲ ለማቅናት መስማማቱን ሶከር ኢትዮጵያ ያገኘችው መረጃ ይጠቁማል።

ከደቂቃዎች በፊት አጥቂው መሐመድኑር ናስርን ለማስፈረም በመስማማት አዲስ ተጫዋች ወደ ቡድኑ የቀላቀሉት ነገሌዎች አሁን ያሬድ ብሩክን ሁለተኛ ፈራሚ በማድረግ ቡናቸውን ማጠናከር ቀጥለውበታል።