በተጠናቀቀው የውድድር ዘመን ከነገሌ አርሲዎች ጋር ጥሩ ቆይታ ያደረገው የመስመር አጥቂ ውሉን ማራዘሙን ሰምተናል።

በሊጉ በመጡበት ዓመት እስከ መጨረሻው ለዋንጫ በመፎካከር ድንቅ የውድድር ዓመት ያስመለከቱን ነገሌ አርሲዎች ቡድናቸውን ማጠናከሩን ገፍተውበት ዘንድሮ ከቡድኑ ጋር ጥሩ ቆይታ ያደረገውን የመስመር አጥቂውን ሀቢብ ከማልን ውል ማራዘማቸውን አውቀናል።
በኢትዮ ኤሌክትሪክ፣ በአርባምንጭ ከተማ፣ በኢትዮጵያ መድን ፣ በድሬዳዋ ከተማ እና ዘንድሮ በነገሌ አርሲ በሠላሳ ሁለት ጨዋታዎች ላይ ሁለት ሺህ ሃያ ደቂቃዎች ላይ ተሳትፎ በማድረግ ሁለት ጎሎችን በማስቆጠር እና ለጎል የሚሆኑ ኳሶችን አመቻችቶ በማቀበል ጥሩ ጊዜ ማሳለፉ ይታወቃል።

