ኢትዮጵያ ቡና የትላንትናው የኢትዮጵያ መድን እና ሲዳማ ቡና ጨዋታ ይጣራልኝ ሲል ጥያቄውን በደብዳቤ አስገብቷል።
በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የ32ኛ ሳምንት የመጀመሪያ ቀን ጨዋታ በትላንትናው ዕለት ቀን ዘጠኝ ሰዓት ላይ በኢትዮጵያ መድን እና ሲዳማ ቡና መካከል ተደርጎ በመድን አሸናፊነት መጠናቀቁ ይታወሳል።
ይህንን የጨዋታ መርሀግብር ተከትሎ ዛሬ ጨዋታውን እያደረገ የሚገኘው እና ከመሪው ኢትዮጵያ መድን በዘጠኝ ነጥቦች ርቆ ሁለተኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ የቻለው ኢትዮጵያ ቡና በትላንትናው ዕለት የተደረገው ጨዋታ ይጣራልኝ ሲል ኢትዮጵያ ቡና ለፕሪምየር ሊግ አክሲዮን ማህበሩ ደብዳቤ አስገብቷል።
ቡድኑ እንዳሰፈረው ከሆነ በዋንጫ ፉክክሩ ላይ ትልቅ ተፅእኖ የሚያሳድር ከእግር ኳስ ስነ ምግባር እጅግ የራቀ ተግባር ተፈፅሟል ብለን እናምናለን ያሉ ሲሆን አወዳዳሪ አካል በሲዳማ ቡና እና ኢትዮጵያ መድን መካከል የተደረገው ጨዋታ ለሀገራችን የእግር ኳስ ዕድገት ማነቆ የሆነ ተግባራት መኖራቸውን የሚያሳይ ድርጊት መሆኑን ተገንዝቦ የጨዋታውን ሂደት እንደገና ተመልክቶ እና አጣርቶ ለእግር ኳስ ቤተሰቡ እንዲያሳውቅልን ሲሉ ገልፀዋል።
የደብዳቤው ሙሉ ይዘት ከዚህ በታች ቀርቧል