እስከ አሁን አስር አዳዲስ እና አንድ ነባር ተጫዋችን ወደ ስብስቡ ያካተተው ሀዋሳ ከተማ የሁለት አዳዲስ እና የሁለት ነባር ተጫዋቾችን ፊርማም አግኝቷል።
በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ላይ የሚካፈለው ሀዋሳ ከተማ በክረምቱ የዝውውር መስኮት እስከ አሁን የአስር አዳዲስ እንዲሁም ደግሞ የአንድ ነባር ተጫዋቾችን ፊርማ ያገኘ ሲሆን አሁን ደግሞ ሁለት ተጨማሪ አዳዲስ እና ሁለት ነባር ተጫዋቾችን የስብስቡ አካል አድርጓል።
አጥቂዋ ሥራ ይርዳው ሀዋሳን ተቀላቅላለች። ከኢትዮጵያ ቡና ከተገኘች በኋላ ለድሬዳዋ ከተማ ፣ መቻል ፣ ኢትዮ ኤሌክትሪክ እና የተጠናቀቀውን ዓመት በአርባምንጭ ከተማ ጀምራ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ካጠናቀቀች በኋላ ቀጣዩ መዳረሻዋ ሀዋሳ ሆኗል። ሌላኛዋ የቡድኑ ፈራሚ ግብ ጠባቂዋ አይናለም ሽታ ናት። በድሬዳዋ ከተማ እና ላለፉት ተከታታይ ዓመታት ደግሞ በአዲስ አበባ ቆይታን ካደረገች በኋላ በይፋ አዲሷ የሀዋሳ ተጫዋች ሆናለች።
ከአዳዲሶቹ ተጫዋቾች በተጨማሪ ክለቡ የአምበሏን እና የመስመር ተከላካዩዋን ምህረት መለሠ እና ጥሩ ዓመትን ያሳለፈችውን የተከላካይ አማካዩዋን ፀጋ ንጉሤን ውል ለተጨማሪ ዓመት አራዝሟል።