ፈቱዲን ጀማል ጦሩን ለመቀላቀል ተስማማ

ፈቱዲን ጀማል ጦሩን ለመቀላቀል ተስማማ

ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር የሊጉን ዋንጫ በአምበልነት ያነሳው የተከላካይ መስመር ተጫዋች ወደ ሌላኛው የሊጉ ክለብ ለማምራት ስምምነት ላይ ደርሷል።

በአሠልጣኝ ሙሉጌታ ምህረት የሚመራው መቻል በ2018 የውድድር ዓመት ተጠናክሮ ለመቅረብ በስፋት በዝውውር መስኮቱ ተሳትፎ እያደረገ እንደሚገኝ ይታወቃል። ከተከላካይ እስከ አጥቂ መስመር ድረስ አዳዲስ ተጫዋቾችን ወደ ስብስቡ የቀላቀለው መቻል አሁን ደግሞ የኋላ መስመሩን ለማጠናከር ተጨማሪ ተጫዋች ማምጣቱን ሶከር ኢትዮጵያ ያገኘችው መረጃ ያመላክታል።

መቻልን ለመቀላቀል የተስማማው ተጫዋች ፈቱዲን ጀማል ነው። ያለፉትን ሁለት የውድድር ዓመታት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቤት ያሳለፈው የቀድሞ የባህር ዳር ከተማ፣ ሲዳማ ቡና፣ ኢትዮጵያ ቡና እና ወላይታ ድቻ ተጫዋች የሊጉን ዋንጫ በአንበልነት ካነሳበት ባንክ በመውጣት ከበርካታ የሊጉ ክለቦች ጋር ከተደራደረ በኋላ መዳረሻውን መቻል አድርጓል።

ከመቻል ጋር በተያያዘ ዜና ቡድኑን ለመቀላቀል ተስማምቶ የነበረው መሳይ ጳውሎስ ዝውውሩ እንዳልተሳካ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።