ናትናኤል ዘለቀ ወደ አዲስ አዳጊዎቹ ለማምራት ከጫፍ ደርሷል

ናትናኤል ዘለቀ ወደ አዲስ አዳጊዎቹ ለማምራት ከጫፍ ደርሷል

በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት በቢጫ ለባሾቹ ቤት ቆይታ የነበረው ናትናኤል ዘለቀ አዲስ አዳጊዎቹን ለመቀላቀል ተስማምቷል።

የ2018 የውድድር ዘመን የመክፈቻ ጨዋታን በኢትዮ ኤሌክትሪክ በመሸነፍ ሊጉን የጀመሩት ሸገር ከተማዎች የአማካይ ተከላካዩን ናትናኤል ዘለቀን ለማስፈረም መቃረባቸውን አውቀናል።

ከፈረሰኞቹ ጋር በአስራ አራት ዓመታት ስኬታማ ቆይታ ስድስት የፕሪምየር ሊግ ዋንጫን ማንሳት የቻለው ናትናኤል ባሳለፍነው ዓመት በወልዋሎ አዲግራት ያሳለፈ ሲሆን በእግርኳስ ህይወቱ ሦስተኛ ክለቡ ወደ ሆነው ሸገር ከተማ ማምራቱ ታውቋል።