ባለፈው የውድድር ዓመት በመቐለ 70 እንደርታ ቆይታ የነበረው ተጫዋች አዲስ ክለብ ተቀላቀለ።
በሁለተኛው የጨዋታ ሳምንት ላይ በፋሲል ከነማ የሁለት ለባዶ ሽንፈት ከገጠማቸው በአሰልጣኝ ግርማ ታደሰ የሚመሩት ወልዋሎዎች አማካዩ ያሬድ ከበደን አስፈረሙ። በ2009 አክሱም ከተማን በመልቀቅ መቐለ 70 እንደርታን ተቀላቅሎ በቡድኑ የአምስት ዓመታት ቆይታ በማድረግ ከምዓም አናብስቱ ጋር የሊጉን ዋንጫ ያሳካው ተጫዋቹ በሲዳማ ቡና እንዲሁም በመቻል የአንድ ዓመት ቆይታ በማድረግ በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት ዳግም ወደ መቐለ 70 እንደርታ ተመልሶ በክለቡ መለያ በ29 ጨዋታዎች ተሳትፎ ማድረጉ የሚታወስ ሲሆን አሁን ደግሞ ወደ ወልዋሎ አምርቷል።