የግራ መስመር ተከላካዩ አዲስ ክለብ ተቀላቀለ

የግራ መስመር ተከላካዩ አዲስ ክለብ ተቀላቀለ

ባለፈው ዓመት በሲዳማ ቡና ቆይታ የነበረው ደስታ ዮሐንስ አዲስ ክለብ አግኝቷል

በአሰልጣኝ ጌታቸው ዳዊት የሚመራው እና ቀደም ብሎ ተመስገን ተስፋዬ እና ብሩክ ቃልቦሬን ያስፈረመው መቐለ 70 እንደርታ አሁን ደግሞ የግራ መስመር ተከላካዩ ደስታ ዮሐንስ አስፈርሟል።

ባለፉት ሁለት የውድድር ዓመታት በሲዳማ ቡና ቆይታ የነበረው ተጫዋቹ ከዚህ ቀደም በአሳዳጊ ክለቡ ሀዋሳ ከተማ፣ አዳማ ከተማ፣ እንዲሁም በሲዳማ ቡናና በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን መጫወቱ የሚታወስ ሲሆን አሁን ደግሞ ከሲዳማ ቡና ጋር የነበረውን ውል መጠናቀቁን ተከትሎ ማረፍያው መቐለ 70 እንደርታ ሆኗል።