አቤል እንዳለ አዲስ ክለብ ተቀላቀለ

አቤል እንዳለ አዲስ ክለብ ተቀላቀለ

ባለፉት ሁለት ዓመታት በፋሲል ከነማ ቆይታ የነበረው አማካዩ አቤል እንዳለ ወደ ሌላ የሊጉ ክለብ አምርቷል

በአሰልጣኝ ዳንኤል ፀሐዬ የሚመሩት ሽረ ምድረ ገነቶች አሁን ደግሞ ባለፉት ሁለት ዓመታት በፋሲል ከነማ ቆይታ የነበረው አማካዩ አቤል እንዳለ አስፈርመዋል። በኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ የእግርኳስ ህይወቱን የጀመረው አማካዩ ቀጥሎ በደደቢት፣ በቅዱስ ጊዮርጊስ፣ በኢትዮጵያ ቡና እንዲሁም በሲዳማ ቡናና ፋሲል ከነማ መጫወቱ የሚታወስ ሲሆን አሁን ደግሞ በ2011 በደደቢት ካሰለጠኑት አሰልጣኝ ዳንኤል ፀሐዬ ጋር በጋራ ለመስራት ወደ ሽረ ምድረ ገነት አምርቷል።