ኢትዮጵያዊ አማካይ እና የአሜሪካው ክለብ ተለያይተዋል።
ከ2016 ዓ.ም የካቲት ወር ጀምሮ ላለፈው አንድ ዓመት ከ9 ወር መቀመጫውን በሊዝበርግ ቨርጂንያ ባደረገውና በUCL Championsip በሚካፈለው ሎዶን ዩናይትድ በመጫወት ላይ የቆየው ኢትዮጵያዊው አማካይ ሱራፌል ዳኛቸው ከአሜሪካው ክለቡ መለያየቱን ክለቡ አስታውቋል።

ክለቡ ዛሬ በአዲሱ የውድድር ዓመት የሚካፈሉትን የቡድኑ አባላት ይፋ ባደረገበት ዜና ሱራፌል ዳኛቸውን ጨምሮ ከአስራ ሁለት ተጫዋቾች ጋር መለያየቱን ይፋ አድርጓል። ፈጣሪው አማካይ ከፋሲል ከነማ ጋር ድንቅ ዓመታት ካሳለፈ በኋላ ወደ አሜሪካው ክለብ ቢያመራም በተለያዩ ምክንያቶች በቂ ግልጋሎት መስጠት አልቻለም።



