በወገኔ ገዛኸኝ ዝውውር አዲስ ነገር ተሰምቷል

በወገኔ ገዛኸኝ ዝውውር አዲስ ነገር ተሰምቷል


ከሰሞኑ ወደ በግብፅ ሊያቀና እንደሆነ በስፋት የተነገረው ወገኔ ገዛኸኝ በተመለከተ አዲስ ነገር ተሰምቷል

ከቀናት በፊት የኢትዮጵያ መድኑ አማካይ ወገኔ ገዛኸኝ በግብፅ ክለብ ሞካውሎን አል ዓረብ የሁለት ዓመት ተኩል ኮንትራት እንደቀረበለት እና በቀናት ውስጥ ወደ ስፍራው ሊያቀና እንደሚችል እንዲሁም የግብፁ ክለብ አማካዩን በነፃ ለማዘዋወር መፈለጉና የተጫዋቹ ባለቤት ኢትዮጵያ መድን ጥያቄውን ውድቅ የሚያደርግበት ዕድል የሰፋ እንደሆነ በመጥቀስ ክለቡ እና ተጫዋቹ ለመነጋገር ቀጠሮ መያዛቸውን መግለፃችን ይታወሳል።

አሁን በተሰማው ዜና ደግሞ የግብፅ ክለብ ሞካውሎን አል ዓረብ ስፖርት ክለብ ከዚህ ቀደም ያቀረበውን የነፃ ዝውውር ጥያቄ በማሻሻል ሰላሣ ሺህ ዶላር ውል መፍረሻ እንዲሁም ከቀጣይ የወገኔ ዝውውር 10% ክፍያ ለኢትዮጵያ መድን ለመፈፀም ከፍተኛ ጥረት ቢያደርግም ክለቡ ካለበት ወቅታዊ ሁኔታ አንፃር ተጫዋቹን ማጣት ከባድ መሆኑን ከግምት ውስጥ በማስገባት የዝውውሩ ጥያቄ እንዳልተቀበለው ዛሬ ለፈላጊው ክለብ አል ዓረብ ስፖርት ክለብ በላከው ደብዳቤ አሳውቋል።

ይህን ተከትሎ ወገኔ ወደ ግብፅ ለመጓዝ ከፍተኛ ፍላጎት ቢያሳይም ውስብስብ በሆነ ሁኔታ ዝውውር በክለቡ ባለቤት ፍቃደኛ ባለመሆን ሳይሳካ መቅረቱ እርግጥ ሆኗል።