መቻል ከስድስት ተጫዋቾች ጋር ተለያይቶ ሁለት አዳዲስ ተጫዋቾች አስፈርሟል

መቻል ከስድስት ተጫዋቾች ጋር ተለያይቶ ሁለት አዳዲስ ተጫዋቾች አስፈርሟል

በአሠልጣኝ ሙሉጌታ ምህረት የሚመራው መቻል በዝውውሩ ስድስት ተጫዋቾችን ከቀነሰ በኋላ በምትኩ ሁለት አዳዲስ ተጫዋቾች የግሉ አድርጓል

 

በሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የ22 ሳምንታት ጉዞ 34 ነጥቦችን በመሰብሰብ አራተኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠው መቻል በውድድር ዓመት አጋማሽ የዝውውር መስኮት ከስድስት ተጫዋቾች ጋር ከተለያየ በኋላ ሁለት አዳዲስ ተጫዋቾችን ማስፈረሙ ታውቋል። ክለቡ ከዮሴፍ ታረቀኝ፣ ደሳለኝ ከተማ፣ ነስረዲን ኃይሉ፣ ቢኒያም ጎዳን፣ ተመስገን ካሱ እና ጳውሎስ መርጊያ ጋር በስምምነት ከተለያየ በኋላ በለቀቁት ምትክ ስብስቡን በሁለት ተጫዋቾች ለማጠናከር ሞክሯል።

ቡድኑን የተቀላቀለው የመጀመሪያው ተጫዋች ሳምሶን ጥላሁን ነው። የቀድሞ የቅዱስ ጊዮርጊስ፣ ኢትዮጵያ ቡና፣ ባህር ዳር ከተማ፣ ሀዲያ ሆሳዕና እና ወልቂጤ ከተማ ተጫዋች የነበረው አማካዩ ዳግም ወደ ሊጉ የተመለሰበትን ዝውውር አከናውኗል።
ሁለተኛው ተጫዋች ደግሞ ተከላካዩ ሚኪያስ ካሣሁን ነው። የቀድሞ የድሬዳዋ ከተማ ተጫዋች የነበረው ሚኪያስ ያለፉትን ሦስት ዓመታት በኢትዮ ኤሌክትሪ ቆይታ ካደረገ በኋላ ወደ መቻል አምርቷል።