የ23ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ዛሬም መደረጋቸውን ሲቀጥሉ ባህር ዳር ከተማ ከ ሸገር ከተማ እንዲሁም ሀዲያ ሆሳዕና ከ ኢትዮጵያ መድን ነጥብ ተጋርተዋል።

ባህር ዳር ከተማ ከ ነገሌ አርሲ
በኳስ ቁጥጥር ረገድ ሁለቱም ቡድኖች ተመጣጣኝ በነበሩበት በመጀመርያው አጋማሽ በባህርዳር ከተማ በኩል በአንተነህ ተፈራ እና በወንድወሰን በለጠ ሙከራዎችን ማድረግ የቻሉ ሲሆን በግብ ጠባቂው ጥረት ግብ ከመሆን ድነዋል። በአንጻሩ ነገሌ አርሲዎች ምንም አይነት የግብ ሙከራዎችን ማድረግ ያልቻሉ ሲሆን በኳስ ቁጥጥሩ ረገድ ግን በመጠኑም ቢሆን ተሽለው ተገኝተው ነበር። ይህንን ተከትሎም ቡድኖቹ ግቦችን ሳያስመለክቱን ወደ መልበሻ ክፍል አምርተዋል።

ሁለተኛው አጋማሽ ላይ ባህር ዳር ከተማዎች ራሳቸውን አሻሽለው የቀረቡ ሲሆን ነገር ግን በሁለቱም ቡድኖች በኩል ረዘም ላሉ ደቂቃዎች የግብ እድሎችን መፍጠር ተስኗቸዋል ተስተውሏል። መደበኛው የጨዋታ ሰዓት ሊጠናቀቅ አምስት ያህል ደቂቃዎች ሲቀሩት በነገሌ አርሲ በኩል እጅግ አስቆጪ ሙከራ በበረከት ወልዴ አማካኝነት ማግኘት ቢችሉም በግብ ጠባቂው ፔፔ ሳይዶ ተመልሶባቸዋል። ይህንንም ተከትሎ ጨዋታው 0-0 በሆነ ውጤት ያለ ግብ ተጠናቋል።
ኢትዮጵያ መድን ከ ሀድያ ሆሳዕና
ሁለት ግቦችን በማስመለከተን የመጀመሪያው አጋማሽ ሁለቱም ቡድኖች ወደ ግብ ቀርበው የግብ እድሎችን በመፍጠር ረገድ ጥሩ የሚባል እንቅስቃሴን ያስመለከቱን ሲሆን ዘጠነኛው ደቂቃ ላይ ሀዲያ ሆሳዕናዎች በብሩክ በየነ ከሳጥን ውጪ ኳስ ሙከራ ማድረግ የቻሉ ሲሆን ከዛ ከሁለት ደቂቃዎች በኋላ ከቀይ መስመር ፀጋአብ ግዛው ያቃበለውን ኳስ ታሪኩ ፀደቀ ወደ ግብነት ቀይሮ ቡድኑን መሪ ማድረግ ችሏል።
ከግቡ መቆጠር በኋላ ወደ ጨዋታ ለመመለስ ጥረት ያደረጉት ኢትዮጵያ መዲኖች በያሬድ ካሳሁን አማካኝነት ለግብ የቀረበ ሙከራ ማድረግ የቻሉ ሲሆን በግብ ጠባቂው ጥረት ግብ ሳይሆን ቀርቷል። ግቦችን ለማግኘት አሁንም ጫና ማድረጋቸውን ቀጥለው የተጫወቱት ኢትዮጵያ መድኖች 30ኛው ደቂቃ ላይ መነሻውን ከመዓዘን ያደረገውን ኳስ አማኑኤል ኤርቦ በግንባሩ በመግጨት ግብ አስቆጥሮ ቡድኑን አቻ ማድረግ ችሏል።

ሁለተኛው አጋማሽ ላይ ሁለቱም ቡድኖች ጥንቃቄን ምርጫቸው በማድረግ ኳሶችን ይዘው ለመጫወት ጥረት አድርገዋል። በዚህም ምክንያት ረዘም ያሉ ደቂቃዎችን ያለ ሙከራ ሲያስመለክቱን 75ኛው ደቂቃ ላይ ኢትዮጵያ መደኖች በሳሙኤል ሳሊሶ አማካኝነት ሙከራ ሲያደርጉ ከአንድ ደቂቃ በኋላ 76ኛው ደቂቃ ላይ ደግሞ ሀዲያ ሆሳዕናዎች በብሩክ በየነ የግንባር ኳስ ግብ ለማግኘት የቀረቡ ቢሆንም ነገር ግን የሞከረው ኳስ የግቡን ቋሚ ከዚያም የግቡን አግዳሚ ገጭቶ ግብ ሳይሆን ቀርቷል ይህም ለሀዲያ ሆሳናዎች በጣም አስቆጪ ሙከራ ነበር። ጨዋታውም ተጨማሪ ግቦችን ሳያስመለክተን አንድ ለአንድ በሆነ ውጤት ተጠናቋል።

