አዲስ አበባ ላይ የሚደረጉ የ27ኛው ሳምንት ጨዋታዎች የት ስታድየም ይከናወናሉ ?

አዲስ አበባ ላይ የሚደረጉ የ27ኛው ሳምንት ጨዋታዎች የት ስታድየም ይከናወናሉ ?

በአዲስ አበባ ስታዲየም የመሮጫ ትራክ ስራ ምክንያት በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ከተደረጉት የ25 እና 26ኛ ሳምንት የሊጉ ጨዋታዎች በኋላ ቀጣይ የጨዋታ ሳምንት የት ስታዲየም እንደሚደረግ ለማጣራት ሞክረናል

የሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች ከ25 ሳምንት እስከ 28ኛ ሳምንት ድረስ አዲስ አበባ እና ሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ስታዲየሞች ላይ እንደሚደረጉ ቀደም ብሎ የሊጉ የበላይ አካል መረጃ አውጥቶ የነበረ ሲሆን የአዲስ አበባ ስታዲየም የመሮጫ ትራክ ስራ አለመጠናቀቁን ተከትሎ ግን በመዲናው የሚደረጉ ጨዋታዎች በአበበ ቢቂላ ስታዲየም እየተደረጉ እንደሆነ ይታወቃል። የመሮጫ ትራኩ ማለቅ ከተሰማ በኋላ ደግሞ የ27 እና 28ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ወደ አንጋፋው ስታዲየም ይመለሳሉ የሚሉ ሀሳቦች ሲሰሙ ቢቆዩም የ27ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ግን እዛው አበበ ቢቂላ ስታዲየም ሊደረጉ እንደሚችሉ የደረሱን መረጃዎች ያመላክታሉ።

ከ27ኛ ሳምንት በኋላ የሚደረጉት የ28ኛ ሳምንት ጨዋታዎችን ጨምሮ የሸገር ደርቢ ፍልሚያ ግን ወደ አዲስ አበባ ስታዲየም እንደሚመለስ የሰማን ሲሆን አክሲዮን ማህበሩም የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ምላሽን ተከትሎ የውድድር ቦታውን ከውድድሩ መጀመር በፊት ያሳውቃል ተብሎ ይጠበቃል።